በሶሪያ የባህር ጠረፍ ላይ የስደተኞች ጀልባ ሰጥማ ቢያንስ 94 ሰዎች ሞቱ
ተሳፍረው ከነበሩት መካከል ህጻናትና አረጋውያን እንደሚገኑበት ተገልጿል
ተስፍረው የነበሩት ስደተኞች ከሊባኖስ፣ከሶሪያ እና ከፍሊስጤም የመጡ ናቸው
ከሊባኖስ የመጡ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በሶሪያ ባህር ዳርቻ ሰጥማለች፡፡
በመስጠም አደጋው ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች ውስጥ የ17 ሰዎች አስከሬን ቅዳሜ እለት መገኘቱን የሶሪያ መንግስት ቴሌቪዥን አስታወቀ።
ከሊባኖስ፣ ከሶሪያ እና ከፍልስጤም የመጡ ስደተኞችን አሳፍራ የነበረች ትንሽ ጀልባ ከሶሪያ ታርቱስ ወደብ ከሊባኖስ ትሪፖሊ በስተሰሜን 30 ማይል ርቀት ላይ ወደ ባህር ስትጓዝ መስጧን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ተሳፍረው ከነበሩት መካከል ህጻናትና አረጋውያን እንደሚገኙበት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር "ልብ የሚሰብር አሳዛኝ" ተብለው ከሚጠሩት በምስራቅ ሜዲትራኒያን ከሚከሰቱ የመርከብ አደጋዎች አንዱ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡