ስትፈለግ የነበረችው ባህር ስርጓጇ ጀልባ ፈንድታ ሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወታቸው አለፈ
ሰዎቹን በህይወት ለማዳን ሲደረግ የነበረው የአምስት ቀናት ፍለጋም አብቅቷል
ከካናዳ መርከብ የተላከ በሮቦት አማካኝነት ጠልቆ በገባ መሳሪያ ከባህር ገጽ 488 ሜትር ርቀት ላይ ቲታን የፈነዳችበትን ቦታ ማግኘቱ ተገልጿል
ከ100 አመታት በፊት የሰጠመችውን የታይታኒክ መርከብ ለማየት ተንቀሳቅሰው የነበሩ አምስት ሰዎች የተሳፈሩባት ቲታን የተሰኘችው ባህር ሰርጓጅ ጀልባ አደጋኛ በሆነ ሁኔታ ፈንድታ ህይወታቸው ማለፉን የአሜሪካ የድንበር ጠባቂ አስታውቋል።
ሰዎቹን በህይወት ለማዳን ሲደረግ የነበረው የአምስት ቀናት ፍለጋም አብቅቷል።
ቲታኗን የመፈለግ ስራው ይዛው የነበረው ለ96 ሰአታት እንደሚበቃ የተገመተው የኦክስጅን መጠን በትናንትናው እለት ማለቁ ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ ደርሶ ነበር።
ከካናዳ መርከብ የተላከ በሮቦት አማካኝነት ጠልቆ በገባ መሳሪያ ከባህር ገጽ 488 ሜትር ርቀት ላይ ቲታን የፈነዳችበትን ቦታ በሰሜን አትላንቲክ ጫፍ ማግኘቱን የአሜሪካ ድንበር ጥበቃ አዛዥ አድሚራል ጆን ማጉዋር ተናግረዋል።
የድንበር ጥበቃ ባለስልጣናት እንደገለጹት 6.7 ሜትር ርዝመት ካላት ቲታን አምስት ትላልል ስብባሪዎች ተገኝተዋል።
ባለስለጣናቱ በቦታው የሰው አካል ስለመገኘቱ ያሉት ነገር የለም።
"ይህ ሰብርባሪው ያለበት ቦታ ሰርጓጇ ጀልባ በአደገኛ ሁኔታ ከፈነዳችበት ጋር ተመሳሳይ ነው" ብለዋል ማጉዋር።
ቲታን የሚያመርተው ድርጅት ኦሽንጌት፣ የድንበር ጥበቃ ባለስልጣናት ከመናገራቸው ቀደም ብሎ ቲታንን ሲያበር የነበረውን ሰው ጨምሮ በህይወት የተረፈ አለመኖሩን ገልጾ ነበር።
በፈረንጆቹ 1912 ከበረዶ ጋር ተጋጭታ በሰጠመችው የታይታኒክ መርከብ ላይ የነበሩ 1500 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።ከካናዳ መርከብ የተላከ በሮቦት አማካኝነት ጠልቆ በገባ መሳሪያ ከባህር ገጽ 488 ሜትር ርቀት ላይ ቲታን የፈነዳችበትን ቦታ ማግኘቱ ተገልጿል