ልዩልዩ
በቱኒዚያ በደረስ የጀልባ መስጠም አደጋ የ23 ስደተኞች ህይወት አለፈ
ስደተኞቹ ሜድትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያን ለመሻገር ሲሉ ነው አደጋው የደረሰባቸው
የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአቅም በላይ ሰዎችን የጫነች ጀልባ ላይ የነበሩ 70 ስደተኞችን ታድገዋል
በቱኒዚያ ስደተኞችን ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰጥማ የ23 ስደተኞች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።
ስደተኞቹ መነሻቸውን ከሊቢያ በማድረግ ሜድትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያን ለመሻገር ሲሉ አደጋው እንዳጋጠማቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
የቱኒዘያ ቀይ ጨረቃ እንዳስታወቀው ፣ ጀልባዋ 39 ስደተኞችን ጭና በመጓዝ ላይ እያለች ነው ኤስ.ፋክስ በተባለ የቱኒዝያ ወደብ አቅራቢያ የሰጠመችው።
በጀልባዋ ላይ በደረሰው የመስጠም አደጋ የ23 ስደተኞች ህይወት በባህሩ ላይ እያሉ ማለፉንም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።
በስፍራው የነበሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአቅም በላይ 70 ሰዎችን የጫነች ጀልባ ላይ የነበሩ ስደተኞችን ማዳን መቻላቸውንም የቱኒዘያ ቀይ ጨረቃ አስታውቋል።
መነሻቸውን ሊቢያ ያደረጉ በርካታ ስደተኞች ሜድትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያን ለመሻገር ሲሉ ህይታቸውን የሚያጡ ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜያትም ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ይሁን እንጂ መነሻቸውን ከአፍሪካ በማድረግ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በየጊዜው አየጨመረ መሄዱ ነው የሚነገረው።