የቻይናዋ መንኮራኩር ሩቅ ከተባለው የጨረቃ ክፍል ናሙና ይዛ ወደ መሬት ጉዞ ጀመረች
የመንኮራኩሯ ከጨረቃ ናሙና ይዛ መነሳት ቻይና ከሩቅ የጨረቃ ክፍል ናሙና በማምጣት የመጀመሪያ ሀገር ለመሆን እንድትቀርብ አድርጓታል
ቸንጅ-6 የተባለችው የቻይና መንኮራኩር ሩብ ከተባለው የጨረቃ ክፍል ናሙናዎችን ይዛ ወደ መሬት ጉዞ መጀመሯን የቻይና ብሔራዊ የስፔስ አጄንሲ አስታውቋል
ቸንጅ-6 የተባለችው የቻይና መንኮራኩር ሩብ ከተባለው የጨረቃ ክፍል ሉናር ሮክስ ወይም የድንጋይ ናሙናዎችን ይዛ ወደ መሬት ጉዞ መጀመሯን የቻይና ብሔራዊ የስፔስ አጄንሲ አስታውቋል።
የመንኮራኩሯ ከጨረቃ ናሙና ይዛ መነሳት ቻይና ከሩቅ የጨረቃ ክፍል ናሙና በማምጣት የመጀመሪያ ሀገር ለመሆን እንድትቀርብ አድርጓታል።
በሀገሪቱ ሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 7:38(23:38 ጂኤምፒ) ጉዞዋን የጀመረችው መንኮራኩር በፈረንጆቹ ከሰኔ 1-2 በተሳካ ሁኔታ ናሙና የመሰብሰብ ስራዋን አጠናቃለች።
የቻይና ብሔራዊ የስፔስ ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ ቸንጅ-6 "በጨረቃ የሩቅ ክፍል የነበረውን ሙቀት መቋቋም ችላለች።"
ቸንጅ-6 ከቅርብ የጨረቃ ክፍል ናሙና ይዛ ከመጣችው ቸንጅ-5 መንኮራኩር ጋር ሲነጻጸር ከመሬት ከሚደረግ ግንኙነት ውጭ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።
በዚህም ምክንያት መንኮራኩሯ ለምታደርገው ግንኙነት ባለፈው ሚያዝያ ወር ወደ ህዋ የተላከችውን ኪውኪያዎ-2 ሳላይትን ተጠቅማለች።
መንኮራኩሯ ከጨረቃ ገጹ ስር ያለ ናሙና ያወጣችው ድሪል እና ሮቦቲክ ክንድ ተጠቅማ መሆኑን ሮይተርስ ሽንዋን ጠቅሶ ዘግቧል።
መንኮራኩሯ ናሙና ከወሰደች በኋላ የቻይናን ሰንደቅ አላማ ለመጀመሪያ ጊዜ በጨረቃ የሩቅ ክፍል ላይ አውለብልባለች።
ኤጀንሲው መንኮራኩሯ አሁን ላይ በጨረቃ ምህዋር ውስጥ እንደሆነች እና ከልላ መንኮራኩር ጋር እንደምትገናኝ ገልጿል። ናሙና የያዘችው መንኮራኩር ሰኔ 25 አካባቢ መሬት እንደምትደርስ ይጠበቃል።