በሙከራው ጃፓን የአደጋ ማስጠንቀቂያ አውጥታለች
ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈችው ሁለተኛው የስለላ መንኮራኩር ከሸፈ።
ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈችው ሁለተኛው የስለላ መንኮራኩር በድጋሚ መውደቁ ተነግሯል።
የመጀመሪያው የስለላ መንኮራኩር ከሦስት ወራት በፊት ተከስክሶ ባህር ውስጥ መውደቁ ተሰምቷል።
የፒዮንግያንግ መገናኛ ብዙኸን እንደዘገቡት መንኮራኩሩ በሦስተኛው ምዕራፍ ላይ እያለ ሀሙስ ጠዋት ወድቋል።
ደቡብ ኮሪያ መንኮራኩሩ በቻይናና በኮሪያ ሰላጤ በኩል አድርጎ ወደ ዓለም አቀፍ የአየር ክልል መብረሩን አስታውቃለች።
ጃፓን በአንድ ግዛቷ ለ20 ደቂቃ የቆየ የአደጋ ማስጠንቀቂያ በማውጣት፤ ዜጎች ቤት ውስጥ እንዲጠለሉ አዛለች።
ጠቅላይ ሚንስትር ፊዩሞ ከሺዳ ሙከራውን በማውገዝ፤ እርምጃው ከመንግስታቱ ድርጅት ህግ ጋር የሚቃረን ነው ብለዋል።
አሜሪካ በበኩሏ ፒዮንግያንግ ከጸብ አጫሪነት እንትወጣ በመጠየቅ፤ በዲፕሎማሲ እንድትሰለፍ አሳስባለች።
ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሰላይ መንኮራኩር የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመለየትና ጥቃቶችን ለማቀነባበር ሁነኛ ነበር ተብሏል።
የፒዮንግያንግ የጠፈር ኤጀንሲ ጥቅምት ላይ በድጋሚ እንደሚሞክር አስታውቋል።