በአፍሪካ እስካሁን ከ50ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ማእከሉ አስታውቋል
በአፍሪካ እስካሁን ከ50ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ማእከሉ አስታውቋል
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 120 967 መድረሱን የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር አስታውቋል፡፡
ማእከሉ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 50 924 መድረሱን ጠቅሷል፤ በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የሞሆኑ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም መቻላቸው ገልጿል ማእከሉ፡፡
በአፍሪካ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ የተጠቁ ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ግብጽ፣ኢትዮጵያ መሆናቸውን ማእከሉ አመልክቷል፡፡ እንደማእከሉ በደቡባዊ አፍሪካ ያሉት ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሞቱና በተያዙ ሰዎች ብዛት ቀዳሚ ነው፡፡
ሰሜናዊው የአፍሪካ ክፍል ደግሞ ከደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል ቀጥሎ በከፍተኛ ደረጃ መጠቃቱን ማእከሉ ጠቅሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደቡብ አፍሪካ 778 571 ሰዎች ከፍተኛ ተጠቂ አላት፡፡
በላፈው አመት በቻይና ሁቤ ግዛት በቻይና የተቀሰቀሰው የኮሮኛ ቫይረስ ወረርሽኝ መላውን አለም በማዳረስ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስከትሏል፡፡