የቻድ ፕሬዘዳንት እድሪስ ዴቢይ መገደላቸውን በትናንትናው እለት የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል
በቻድ የተካሄደውም 3ኛ ዙር ምርጫ ያሸነፉት የቻድ ፕሬዘዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከጽንፈኞች ጋር እየተዋጋ ያለውን የቻድ ጦር በመጎብኘት ላይ እያሉ ቆስለው ህይወታቸው እንዳለፈ መገለጹ ይታወሳል። አሁን ላይ ቻድን እየመሩ ያሉት የሟቹ ፕሬዘዳነት ኢድሪስ ዴቢ ወንድ ልጅ ማሃማት እድሪስ ዴቢ ናቸው።
የ37 ዓመት አድሜ ያለው ወጣቱ ባለ አራት ኮኮብ ማዕረግ መሃማት 15 የጠር መሪዎች አባላት ያሉት የወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ማቋቋማቸውን ዥንዋ ዘግቧል።
በወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒሰትሩ ሱለይማን አባካር እና የቀድሞው ደህንነት እና የአገር ግዛት ሚኒሰተሩ ጀነራል ማሃማት እስማኤል ተካተውበታል።
በምክር ቤቱ ውስጥ ብዙዎቹ አባላት በቀድሞው ፕሬዘዳንት እድሪስ ዴቢ የስልጣን ዘመን በተለያዩ ወታደራዊ ተቋማት ላይ በሰልጣን ላይ የቆዩ እንደሆኑም ዘገባው ጠቁሟል። 15 አባላት ያሉት ይህ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ለቀጣዮቹ 18 ወራት ቻድን እንደሚመራ የተገለጸ ሲሆን ምርጫ ከተደረገ በኋላ ምክር ቤቱ ስልጣኑን በምርጫ ላሸነፈ ፓርቲ አሳልፎ ይሰጣልም ተብሏል።