የቺቺኑ መሪ እስረኛ በደበደበው ልጃቸው እንደሚኮሩ ተናገሩ
ካዲሮቭ ይህን ያሉት ልጃው አዳም ካኪ የለበሰ ሰው ደብድቦ መሬት ላይ ሲጥል የሚያሳይ ቪዲዮ አስከትለው በለቀቁበት የቴሌግራም መልእክታቸው ነው
"ደብድቦታል። ትክክለኛ ነገር ነው ያደረገው" ብለዋል ካዲሮቭ።
የሩሲያዋ ቺቺን ግዛት መሪ ራምዛን ካዲሮቭ ቁርአን በማቀጠል የተከሰሰውን ግለሰብ በደበደበው ልጃቸው እንደሚኮሩ ተናግረዋል።
የሩሲያዋ ቺቺኒያ መሪ ራምዛን ከዲሮቭ የራሱን ጦር ማቋቋም እንደሚፈልግ ተናገረ
ካዲሮቭ ይህን ያሉት አዳም የተባለው ልጃቸው ካኪ የለበሰ ሰው ደብድቦ መሬት ላይ ሲጥል የሚያሳይ ቪዲዮ አስከትለው በለቀቁበት የቴሌግራም መልእክታቸው ነው።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ቁልፍ አጋር አድርገው ራሳቸውን የሚያዩት ካዲሮቭ ቪዲዮውን የለቀቁት ባለፈው ወር ችግሩ ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም የሚለውን ጥርጣሬ ግልጽ ለማድረግ ነው ብለዋል።
"ደብድቦታል። ትክክለኛ ነገር ነው ያደረገው" ብለዋል ካዲሮቭ።
"ያለማጋነን አዳም በፈጸመው ድርጊት ኮርቻለሁ" ያሉት ካዲሮቭ ልጁ ክብሩን እና ሀይማኖቱን ለመከላከል የወሰደውን እርምጃ እንደሚያከብሩ ገልጸዋል።
ኒኪታ ዙራቨል የተባለው እስረኛው የደረሰበትን ጥቃት ለሩሲያ እንባጠባቂ ተቋም አቤቱታ አቅርቦ ነበር።
የ46 አመቱ ካዲሮቭ የቺቺን ፕሬዝዳንት ከሆኑበት ከፈረንጆቹ 2007 ጀምሮ በጉልበት እየመሩ ናቸው።
በሶቬት ህብረት መፈራረስ ወቅት ውድመት የደረሰባት እና አብዛኛው ህዝብ ሙስሊም የሆነባት ቺቺን ለመልሶ ግንባታ ከፕሬዝደንት ፑቲን ከፍተኛ እርዳታ እያገች ነው።
ከዲሮብ የሚመራው ጦር ሩሲያ በዩክሬን እያደረገችው ባለችው ጦርነት መሳተፉ ይታወሳል።