ሩሲያ 'የጥቁር ባህር ስምምነትን' ለማደስ የሚደረገው ጥረት የማይሳካ ነው አለች
ላቭሮቭ ይህን ያሉት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት በአካል በተገኙበት እና ምዕራባውያን አጋሮቻቸው ለኪቭ ድጋፍ በሻቱበት የኒው ዮርኩ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው
ላቭሮቭ 193 አባል ሀገራት ባሉት የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በአብዛኛው የአለም ማህበረሰብ እና ለማሸነፍ የቅኝ ግዛት ዘዴን በሚጠቀሙ ጥቂቶች መካከል ትግል እየተካሄደ ነው ብለዋል
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተመድ 'የጥቁር ባህር የእህል ስምምነትን' ለማደስ የሚያደርገው ጥረት የማይሳካ መሆኑን ተናገሩ።
በማድግ ላይ ያሉ ሀገራትን ድጋፍ የሚሹት አሜሪካ እና አውሮፖ በተቀረው አለም ላይ ንቀት እያሳዩ ነው ያሉት ላቭሮቭ ሩሲያ ተመድ ስምምነቱን ለማደስ የሚያደርገውን ጥረት ባትቃወምም በቅርቡ ያቀረበው ምክረሃሳብ ግን እውነት የራቀ ነው ብለዋል።
ላቭሮቭ ይህን ያሉት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት በአካል በተገኙበት እና ምዕራባውያን አጋሮቻቸው ለኪቭ ድጋፍ በሻቱበት የኒው ዮርኩ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።
ላቭሮቭ ከጉባዔው ጎንለጎን ከ30 ሀገራት በላይ ከመጡ ዲፕሎማቶች ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ተመድ ሩሲያ በፈረንጆቹ 2022 በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ አንዳቸው ሌላቸውን ለማሸነፍ በሚያደርጉት ጥረት የምግብ እጥረት ቀውስ እና አዲስ የዲፕሎማቲክ ፍጥጫ ተፈጥሯል የሚል ወቀሳ አቅርቧል።
ላቭሮቭ 193 አባል ሀገራት ባሉት የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በአብዛኛው የአለም ማህበረሰብ እና ለማሸነፍ የቅኝ ግዛት ዘዴን በሚጠቀሙ ጥቂቶች መካከል ትግል እየተካሄደ ነው ብለዋል።
በፈረንጆቹ ሐምሌ2022፣ በቱርክ እና በተመድ አማካንነት የተደረሰው እና ዩክሬን እህሏን በጥቁር ባህር በኩል ወደ ውጭ እንድትልክ ያስቻላት "የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት" ሩሲያ ከስምምነቱ በመውጣቷ ምክንያት ፈርሷል።
ሩሲያ ከስምምነቱ የወጣችው በስምምነቱ መሰረት የምትፈልገው ተፈጻሚ አለመሆኑን በመግለጽ ነበር።
ላቭሮቭ ለተመድ ዋና ጸኃፊ በጻፉት ደብዳቤ ተመድ ያቀረበው ምክረሃሳብ ሊተገበር የማይችል እና የማይሳካ መሆኑን መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።