አሜሪካ የአምስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ በቺቺኒያው መሪ ካዲሮቭ ላይ ማዕቀብ ጣለች
የዋሸንግተን ማዕቀብ ለፕሬዝዳንት ፑቲን ቅርብ በሆኑ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል
የቺቺኒያው መሪ ራምዛን ካዲሮቭ 11 የቤተሰብ አባላት በአሜሪካ አዲስ ማዕቀብ ተጥሎበታል
አሜሪካ የአምስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ በቺቺኒያው መሪ ካዲሮቭ ላይ ማዕቀብ ጣለች፡፡
ከ450 በላይ ቀናትን ያስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አሁንም እልባት ያልተገኘለት ሲሆን ጦርነቱም መልኩን እየቀያየረ ቀጥሏል፡፡
ጦርነቱን ተከትሎም ሩሲያ ወታደሮቿን ከዩክሬን እንድታስወጣ በሚል ከ12 ሺህ በላይ ማዕቀቦች በአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት የተጣለባት ሲሆን ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቅርብ የሆኑ ሰዎችም ማዕቀቦች ትኩረታቸውን አድርገዋል ተብሏል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ ለፕሬዝዳንት ፑቲን ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት የቺቺኒያዋ ራስገዝ አስተዳዳሪ የሆኑት ራምዛን ካዲሮቭ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉ ተገልጿል፡፡
የሩሲያ ነዳጅ ማዕቀብ ቢጣልበትም በከፍተኛ መጠን እየተሸጠ መሆኑ ግርምትን ፈጥራል
አሜሪካ ከዚህ በፊት በካዲሮቭ ላይ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን አሁን ደግሞ የቤተሰቡ አባላት በሆኑ 11 ሰዎች ላይ አዲስ ማዕቀብ እንደተጣለባቸው ተገልጿል፡፡
ካዲሮቭ የዋሸንግተንን ማዕቀብ አስመልክቶ በቴሌግራም ገጹ ላይ እንደገለጸው ማዕቀብ ከተጣለባቸው የቤተሰቡ አባላት መካከል እናቱ እንደተካተቱበት እና በድርጊቱ ማዘኑን ገልጿል፡፡
አይማኒ ካዲሮቭ በመባል የሚታወቁት እናቱ በበጎ አድራጎት ስራ ላይ መሰማራታቸውን የገለጸው እስማኤል ካዲሮቭ የአሜሪካንን ማዕቀብ ተችቷል፡፡
"እኔ አሜሪካንን ጨምሮ በምዕራባዊያን ሀገራት ምንም ሂሳብም ሆነ ንብረት የለኝም የሚለው ካዲሮቭ እናቴ በዚህ ማዕቀብ ውስጥ መካተቷ ያስገርማል፣ ማዕቀቡ አሳፋሪ እና ሞራል ከሌለው አካል የሚጠበቅ ነው" ሲል ለተከታዮቹ አስፍሯል፡፡
የአሜሪካ ማዕቀብ ከካዲሮቭ እናት በተጨማሪም የአምስት ዓመት ሴት ልጅንም አልማረም የተባለ ሲሆን ለማዕቀቡ ምክንያት የተባለው የዩክሬን ህጻናትን በሀይል ወደ ሩሲያ ማጓጓዝ ወንጀል ላይ ተሳትፈዋል በሚል እንደሆነ ተገልጿል፡፡