ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን ማንነት ለይቻለሁ ቢልም እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉ ተገልጿል
በአሜሪካ በዝርፊያ ዙሪያ ዘገባ እየሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞች መዘረፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
በአሜሪካ የቺካጎ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በግዛቲቱ ተፈጸመ የተባለ የዝርፊያ ወንጀል ዙሪያ ለዘገባ ባመሩበት ወቅት ተዘርፈዋል ተብሏል።
ዘራፊዎቹ የፊት መሸፈኛ አድርገው በራሳቸው ተሽከርካሪ በመምጣት የቴሌቪዥን ካሜራ እና ሌሎች ንብረቶችን በያዙት ሽጉጥ አስፈራርተው ወስደዋል ተብሏል።
በሚዲያው የስፓኒሽ ቋንቋ ጋዜጠኞች ንብረት ከመዘረፉ ውጪ አካላዊ ጥቃት እንዳልደረሰባቸውም ተገልጿል።
ይህን ተከትሎ ጋዜጠኞቹ ለዘገባ ለሄዱበት ወንጀል ዝርዝር ዘገባ ያገለግላል የተባለው ምስልም አብሮ ከቪዲዮ ካሜራው ጋር በመዘረፉ ዘገባው አልተሰራም መባሉን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
የቺካጎ ፖሊስ የዘራፊዎቹን ማንነት ለይቻለሁ ያለ ሲሆን የ28 እና 42 ዓመት እድሜ ያላቸው ሰዎች እንደሆኑ አስታውቋል።
ይሁንና ፖሊስ ተጠርጣሪ ዘራፊዎቹን እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳላዋለ ገልጾ በፍለጋ ላይ መሆኑን ገልጿል።
በቺካጎ ግዛት በተደጋጋሚ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።