የኡጋንዳ ሚኒስትር በቤት ክዳን ቆርቆሮ ዝርፊያ ዘብጥያ መውረዳቸው ተነግሯል
የኡጋዳ የክልሎች ሚኒስትር በ14 ሺህ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ዝርፊያ ቅሌት ነው ተጠርጥረው የተያዙት
የሀገሪቱ ም/ፕሬዝዳንትና ጠ/ሚኒስትርን ጨምሮ 10 ከፍተኛ ባለስልጣንት የተሰረቀውን ቆርቆሮ ውስደዋል ተብሏል
የኡጋዳ የክልሎች ሚኒስትር ጎሬቲ ኪቱቱ ከቤት ክዳን ቆርቆሮ ዝርፊያ ቅሌት ጋር በተያያዘ ፋሲካን በእስር ቤት ያሳልፋሉ ተብሏል።
ሚኒስትሯ ለእስር የተዳረጉት በሀገሪቱ የተፈፀመው የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች ዝርፊያ ላይ ተሳትፈዋል በሚል እንደሆነ ቢቢሲ አስነብቧል።
- የዓለም ፍጻሜ ደርሷል በሚል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኡጋንዳዊያን ያንጋቶም እየኖሩ መሆኑ ተገለጸ
- ከ12 ሚስቶች 102 ልጆችን ያገኙት ኡጋንዳዊ የኑሮ ውድነት ቤተሰቤ እንዳይስፋፋ ገድቦታል አሉ
የክልሎች ሚኒስትር ጎሬቲ ኪቱቱ በኡጋንዳ ሰሜን ምስራቅ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የተዘጋጀውን 14 ሺህ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ነውየተጠረጠሩት።
ሚኒስትሯ ባሳለፍነው አርብ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ እስካሁን የጥፋተኝነት ውሰኔ ባሳያልፍባቸውም የዋስትና መብት ግን ከልክሏቸዋል።
10 የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሰረቀውን የቤት ክዳን ቆርቆሮ እንደተቀበሉትም ዘገባው አክሏል።
ቆርቆሮውን ከተቀበሉት ሰዎች መካከልም የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የፓርላማ አፈ ጉባዔ እንዲሁም ሌሎች ሚኒስትሮች ይገኙበታል ነው የተባለው።
የኡጋዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ በመጠየቅ ሌሎችም ባለስልጣናት ቆርቆሮዎቹን እንዲመልሱ ጥሪ ማቅረባቸውም ተነግሯል።
የሀገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባዔ አኒታ የተቀበሉትን የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች መመለሳቸውን ለምክር ቤቱ ተናግረዋል ነው የተባለው።
አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ሚኒስትርም ለፍየሎቻቸው መጠለያ አልብሰውት የበረውን የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች ማንሳታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አስነብበዋል።