የቤጂንግና ሀቫና ግንኙነት ለአሜሪካ ቅርብ የሆነ አዲስ ስጋት ፈጥሯል ተብሏል
ቻይና ከአሜሪካ የፍሎሪዳ ግዛት 160 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በምትገኘው ኩባ የስለላ ጣቢያ ለማቋቋም ሚስጥራዊ ስምምነት ላይ ደርሳለች ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል።
ይህ መሰሉ የስለላ ጣቢያ ቤጂንግ ብዙ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች ከሚኝበ ት ደቡብ ምስራቅ ክልል በኤሌክትሮኒክስ መገናኛዎች እንድትሰበስብ ያ ስችላታል ተብሏል።
እንዲሁም የመርከብ ትራፊክን ለመቆጣጠር ያስችላል ሲል ጋዜጣው ሚስጥራዊ መረጃን የሚያውቁ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሀገራቱ በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የተነገረ ሲሆን፤ ቻይና ለኩባ "በርካታ ቢሊዮን ዶላር" ለጣቢያው እንድትከፍል መደረጉን ጋዜጣው ዘግቧል።
ነገር ግን የአሜሪካ እና የኩባ መንግስታት በሪፖርቱ ላይ ጠንካራ ጥርጣሬ አሳይተዋል።
የዋይት ሀውስ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ ለሮይተርስ "ሪፖርቱን ተመልክተናል። ግን ትክክል አይደለም" ብለዋል።
ነገር ግን ቃል አቀባዩ ትክክር ያልሆነውን ጉዳይ ግለጽ አላደረጉም።
ዋሽንግተን ቻይና ከኩባ ጋር ስላላት ግንኙነት እውነተኛ ስጋት እንዳላት እና በቅርበት እየተከታተለች ነውም ብለዋል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ፓትሪክ ራይደር፤ "ቻይና እና ኩባ አዲስ አይነት የስለላ ጣቢያ እየሰሩ እንደሆነ አናውቅም" ብለዋል።
የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ካርሎስ ፈርናንዴዝ ደ ኮሲዮ ሪፖርቱን "ፌም አ ደገኛ እና መሰረተ ቢስ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
ይህ የአሜሪካ ፈጠራ ነው ሲሉ ዋሽንግተን በደሴቲቱ ላይ የጣለችውንና አስ ርት ዓመታት ያስቆጠረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ምክንያት ለማድረግ ነው ብለዋል ።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ኩባ በላቲን አሜሪካ እና በካሪቢያን አካባቢ ያሉትን ሁሉንም የውጭ ወታደራዊ ኃይሎች እንደማትቀበል ተናግረዋል።
በዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ "ጉዳዩን አናውቅም፤ በ ዚህም ምክንያት አሁን አስተያየት መስጠት አንችልም" ብለዋል።
በሁለቱ በኮሚኒስት መንግስታት የሚመሩ የአሜሪካ ተቀናቃኝ ሀገራት መካከል ያለው ስምምነት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ላይ ስጋት ፈጥሯ ያለ ው ዎል ስትሪት ጆርናል ሲል፤ ለአሜሪካ ቅርብ የሆነ አዲስ ስጋትን ፈጥሯል ብሏል።