አሜሪካ የቻይና ተንሳፋፊ የስለላ ፊኛን በጦር ጄት መትታ ጣለች
የቻይና ተንሳፋፊ ፊኛ ለአንድ ሳምንት ያክል በሜሪካ ቁልፍ ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ስትሰልል ነበር
አሜሪካ ተንሳፋፊ ፊኛውን መትቶ ለመጣል በርካታ ተዋጊ ጄቶችና የአየር ላይ ነዳጅ መሙያ አውሮፕላኖችን አሰማርታ ነበር
ቻይና ተንሳፋፊ ፊኛን በመጠቀም በአሜሪካ ቁልፍ ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ስለላ መፈጸሟ ከሰሞኑ ትልቅ ክስተት ሆኖ ሰንብቷል።
አሜሪካ ሌሊቱን በአሜሪካ ላይ ለስለላ የተላከችውን ግዝፍ የቻይና ተንሳፋፊ ፊኛ ጦር ጄቶቿን በማሰማራት መትታ መጣሏ ተነግሯል
ሰላዩ ተንሳፋፊ ፊኛ በአሜሪካ የውኃ ክልል ላይ በተንሳፋ ፊኛ ተመትቶ መውደቁን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።
አሜሪካ ተንሳፋፊ ፊኛውን መትቶ ለመጣል በርካታ ተዋጊ ጄቶችና የአር ላይ ነዳጅ መሙያ አውሮፕላኖችን ያሰማራች ቢሆንም፤ ኤፍ 12 ጄት በተኮሰው አንድ AIM-9X ሱፐርሶኒክ ሚሳዔል ነው የተመታው።
የቻይና ተንሳፋፊ ፊኛ ለአንድ ሳምንት ያክል በሜሪካ ቁልፍ ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ስትሰልል ነበር መባሉነ ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት ወደ እሰጣ ገባ ገብተዋል።
ክስተቱ ቻይና በአሜሪካ ላይ የሰነዘረችው ጥቃት አካል ነው ያለችው አሜሪካ ጉዳዩ እንዳሳሰባት አስታውቃለች። የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ሲአኤ ሀላፊ የሆኑት ዊሊያም በርንስ በበኩላቸው ቻይና የአሜሪካ ዋነኛ ስጋት ናት ብለዋል።
ቻይና በበኩሏ ክስተቱ “በአንዳች ሃይል የተፈጠረ ተአምር” እንጂ ሆን ተብሎ የተፈጸመ እንዳልሆነም ነው የገለጸችው።
ቤጂንግ ቀደም ብላም ፊኛዎቹን አቅጣጫ ያስቀየረው ያልተጠበቀ ንፋስ መሆኑን መግለጿን ሬውተርስ ዘግቧል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ የአሜሪካ ባለስልጣናት እና የመገናኛ ብዙሃን አጋጣሚውን ቻይናን ለማብጠልጠል መጠቀማቸውን ተቃውሟል።