በሰዓት 218 ኪሎ ሜትር የሚጓዘው አውሮፕላኑ በአንድ በረራ 1,100 ኪሎ ሜትር ርቀት ይጓዛል
ቻይና በራሷ አቅም የሰራችው እና ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራው አውሮፕን የመጀመሪያውን የመካከለኛ ርቀት በረራ ማድረጉ ተገለጸ።
ቻይና በራሷ ያመረተችው የ“AG60E” ኤሌክትሪክ አውሮፕላን ምርቶች ውስጥ የኤሌክትሪክ ስሪት የሆነው “AG60” አውሮፕላን ባሳለፍነው ረቡዕ የመጀመሪያ በረራውን ማድረጉም ተነግሯል።
የኤሌክትሪክ አውሮፕላኑን በረራ የማስጀመር ስነ ስርዓት በምስራቅ ቻይና ዠጂያንግ ግዛት የጂያንዴ ኪያንዳኦሁ አውሮፕላን ማረፊያ መካሄዱን የቻይና አቪዬሽን ኢንደስትሪ የአውሮፕላ ምርቶች ኮርፖሬሽን አስታውቋል።
የኤሌክሪክ አውሮፕላን አምራች ቡድን በምርት ወቅት ከሞተር ምርጫ ጀምሮ፣ የኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ እና የባትሪ መረጣን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን በጥንቃቄ ማከናወናቸው ተገልጿል።
እንዲሁም የአውሮፕላኑ ደህንነት እና በበረራ ወቅት የአየር ላይ ብቁነት ፍተሸ ማናወኑን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
ባለ አንድ ሞተሩ የኤሌክትሪክ አውሮፕላን ሙሉ በሙሉ ከብረት የተሰራ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገውም በ2021 በተካሄደው 13ኛ የቻይና ኤር ሾው ላይ ነበር።
6.9 ሜትር ርዝመት ያለው አውሮፕላኑ የክንዱ ስፋት 8.6 ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ነው።
“AG60E” ኤሌክትሪክ አውሮፕላን በሰዓት 218 ኪሎ ሜትር ይጓዛል የተባለ ሲሆን፤ በአንድ ጊዜም እስከ 1 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ይችላል።
“AG60” አውሮፕላን የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ በረራ ሙከራውን በፈረንጆቹ 2020 ማጠናቀቁን ተከትሎ በ2021 በምስራቅ ቻይና ክልል አስተዳደር የቀላል ስፖርት የአውሮፕላን ሰርተፍኬት እና የምረት ፍቃድ አግኝቷል።