ጃፓናዊት እናት እና ልጇን ከጥቃት ስትከላከል በደረሰባት ጥቃት የሞተችው ቻይናዊ ጀግና ተባለች
እናት እና ልጇን ከጥቃት ስትከላከል በደረሰባት ጥቃት የሞተችው ቻይናዊ ደግና ተባለ
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክስተቱ የሚያጸጽት መሆኑን እና የውጭ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ገልጿል
ጃፓናዊት እናት እና ልጇን ከቢለዋ ጥቃት የታደገችው ቻይናዊት ሴት ሞተች።
አንድ ግለሰብ በጃፓን ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ደጃፍ ላይ በሚገኝ የመኪና ማቆሚያ በጃፓናዊቷ ሴት ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ወቅት፣ ሁ ዩፒንግ የተባለችው ቻይናዊ ጥቃቱን ተከላክላለች።
ሁ ጥቃት አድራሹን ለማስቆም ባደረገችው ጥረት ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሟታል። ድርጊቱን የሰሙ ሰዎች ለሁ በኦንላይን አድናቆታቸውን እያጎረፉ ሲሆን የአካባቢው መንግስትም "የመልካምነት እና የጀግነት ተምሳሌት" የሚል ሽልማት እንደሚሰጣት ገልጿል።
የጃፓን ኢምባሲም ለ ሁ ሀዘኑን ለመግለጽ ሰንደቅ አላማውን ዝቅ አድርጎ እያውለበለበ ነው።
ኢምባሲው የቻይና ማህበራዊ ሚዲያ በሆነው ዌቦ ባሰፈረው መግለጫ ህይወቷ በማለፉ ማዘኑን ገልጿል።
"የሁ ጀግንነት እና ደግነት የቻይናን ህዝብ የሚወክል ነው ብለን እናምናለን። የእሷን መልካም ስራ እንዘክራለን። ነፍሷ በሰላም ይረፍ"ብሏል መግለጫው።
በቻይና ማህበራዊ ሚዲያ የማጽናኛ እና የአድናቆት መልእክቶች በብዛት እየተላለፉ ይገኛሉ።
ከመልእክቶቹ አንዱ "ጃፓናዊ ጓደኞቻችን ስላዳነች እና የቻይናውያንን መልካም ስም ስላስጠብቅሽ፣ ደግነትሽን እና ጀግንነትሽን እናስታውሳለን" ይላል።
"ተራ፣ ጀግና እና ደፋር ቻይናዊት ሴት" ይላል ልላኛው መልእክት።
ባለፈው ሰኞ እለት በነበረው ጥቃት እናት ልጆቹ ጃፓናውያን ጥቃት ቢደርሰባቸው፣ ጥቃቱ ለህይወታቸው የሚያሰጋ አይደለም።
የ52 አመቱ ቻይናዊ ተጠርጣሪ በቦታው በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህ ጥቃት የተፈጸመው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አራት የአሜሪካ የዩኒቨርስቲ መምህራን በጂሊን ፓርክ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ነው።የቻይና ባለስልጣናት ሁለቱ ክስተቶች የተለያዩ ናቸው ይላሉ።
ግሎባል ታይምስ የተባለው የቻይና ጋዜጣ በአርብ እትሙ የሁን ጀግንነት አወድሶ "ቻይና አሁንም በማያሻማ መልኩ በአለም ሰላማዊ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ነች" ብሏል።
በሱዙ የተከሰተው ጥቃት በጃፓናውያን ዘንድ ስጋት ፈጥሯል፣ የጂፓን ኢምባሲም ማስጠንቀቂያ እንዲያወጣ አስገድዶታል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክስተቱ የሚያጸጽት መሆኑን እና የውጭ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ገልጿል።