አንድ ግለሰብ የቻይናን ወታደራዊ ሚስጥር የያዙ መጻህፍት ከአንድ ዶላር ባነሰ ዋጋ መግዛታቸው ተነገረ
የቻይና የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስቴር በማህበራዊ ሚዲያ ባወጣው መግለጫ ደውለው ያሳወቁትን ግለሰብ አመስግኗል
ቻይና ውስጥ አንድ ግለሰብ የቻይናን ወታደራዊ ሚስጥር የያዙ አራት መጻህፍትን ከአንድ ዶላር ባነሰ ዋጋ የገዙበት አጋጣሚ አነጋጋሪ ሆኗል
አንድ ግለሰብ የቻይናን ወታደራዊ ሚስጥር የያዙ መጻህፍት ከአንድ ዶላር ባነሰ ዋጋ መግዛታቸው ተነገረ።
ቻይና ውስጥ አንድ ግለሰብ በአካባቢው ከሚገኝ ቆሻሻ ማስወገጃ ወይም ሪሳይክል ሴንተር ከአንድ ዶላር ባነሰ ዋጋ የገዛቸው አራት መጻህፍት የቻይናን ወታደራዊ ሚስጥር የያዙ መሆናቸው አነጋጋሪ ሆኗል። መጻህፍቱ ሚስጥራዊ ወታደራዊ ሰነዶችን ይዘዋል ተብሏል።
የቻይና የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስቴር በማህበራዊ ሚዲያ ባወጣው መግለጫ ደውለው ያሳወቁትን ግለሰብ ባለፈው ሀሙስ እለት ማመስገኑን ኤፒ ዘግቧል።
በቤተሰብ ስማቸው ዛንግ እንደሚባሉ የገለጸው ሚኒስቴሩ መጽሀፍቱ የያዙት ሰነድ ስለምን እንደሚያወሳ ግልጽ አላደረገም።
"ዛንግ የሀገሪቱን ወታደራዊ ሚስጥር እንደገዙ አስበው ወደ መጽሀፍቱን ወደ ቤታቸው ወስደዋቸዋል" ያለው ሚኒስቴር ሌላ አላማ ባለው ሰው እጅ ገብተው ቢሆን ኖሮ ጉዳቱ ከፍተኛ ይሆን ነበር ሲል ገልጿል።
የሚኒስቴሩ መግለጫ ቢያንስ በሁለት ተወዳጅ የቻይና የዜና ድረ ገጾች ተለቆ ብዙዎች ተነጋግረውበታል። ለጉዳዩ የተሰጠው ሽፋን ብሔራዊ ደህንነት ከአሜሪካ ጋር ፎጥጫ ውስጥ ለገባቸው ቻይና ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ግንዛቤ ለማስጨበጭ አላማ ያለው ነው ተብሏል።
ሚኒስቴሩ እንገለጸው መጻህፍቱን የገዛው ግለሰብ የቀድሞ የመንግስት ድርጅት ሰራተኛ ሲሆኑ ወታራዊ ጋዜጦችን እና መጽሄቶችን መሰብሰብ የሚወድ ነው።
ግለሰቡ በቆሻሻ ማስወገጃው ጣቢያ ሁለት ሻንጣ ሙሉ አዳዲስ መጽሀፍትን ማግኘቱን እና ለአራቱ መጻህፍት ስድስት ዩዋን መክፈሉን ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ እንዳለው ዛንግ ይህን ካሳወቁ በኋላ የደህንነት ሰራተኞች ወደ ጣቢያ በፍጥነት ሄደዋል። ምርመራ ከተደረገ በኋላ ሁለት ወታራዊ ሰራተኞች መቅደድ ሲገባቸው 30 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ 200 መቶ መጻህፍትን በ2.75 ዶላር ድጋሚ ጥቅም ላይ ለሚያውለው ማዕከል በመሸጥ ክስ ተመስርቶባቸዋል።
የደህንነት ሰራኞቹ መጽሀፍቱን መያዛቸውን እና እንዲህ አይነት ሰነዶች የሚባክኑበት ክፍተት መወጋቱንም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል።