በአለማችን ትልቁ ሰው ሰራሽ ደሴት ላይ ቻይና እያስገነባች የምትገኝው አውሮፕላን ማረፍያ
ኤርፖርቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በአመት 540 ሺህ በረራዎችን እና 80 ሚሊየን ተጓዦችን በማስተናገድ በግዝፈቱ ቀዳሚ ይሆናል
በአሁኑ ወቅት በቻይና 200 አውሮፕላን ማረፊያዎች ሲኖሩ የገበያውን ፍላጎት ለማሟላት በ2035 450 ማረፊያዎች ያስገልጓታል
ቻይና አዳዲስ ፈጠራዎችን በማስተዋወቅ እና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመግንባት በአለም ቀዳሚ የምትሆንበትን አዲስ ፕሮጀክት እየገነባች ትገኛለች፡፡
ሀገሪቱ በአለማችን ግዙፍ በተባለው ሰው ሰራሽ ደሴት ላይ በግዝፈቱ ተወዳዳሪ አይኖረውም የተባለውን ኤርፖርት እውን ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምራለች፡፡
አራት ትላቅ የአውሮፕላን መንደርደርያዎችን እና ማረፊያዎችን ይይዛል የተባለው የደሴት ላይ ኤርፖርት 900 ሺ ስኩየር መሬት ላይ ያረፈ የመንገደኞች ማስተናገጃ (ተርሚናል) ይይዛል፡፡
በሂደት 20 ስኩየር ኪሎሜተር ስፋት ለመሸፈን ያቀደው የደሴት ኤርፖርት የሆንግኮንግ አለም አቀፍ ኤርፖርት እና የጃፓኑን ካንሳይ ኤርፖርት በመብለጥ ቀዳሚ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም በአመት 80 ሚሊየን መንገደኞችን እና 540 ሺ በረራዎችን የሚያስተናግድ አቅም ይኖረዋልም ተብሏል፡፡
7.5 ሚሊየን ሰዎች በሚኖሩበት ዳሊያን በተሰኝ ከተማ ላይ የሚገነባው አውሮፕላን ማረፊያ ለጃፓን እና ደቡብ ኮርያ ካለው ቅርበት አንጻር ከፍተኛ የትራንስፖርት መነሀሪያ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በከተማዋ ለ100 አመታት ያገለገለው የዳሊያን ጆሽዊዢ ኤርፖርት ለበርካታ ጊዜ ማስፋፋፍያ ቢደረግለትም አሁን ላይ ያሉትን ደንበኞች ወይም ተጓዦች ማስተናገድ የሚችልበት አቅም ላይ እንደማይገኝ ሲኤንኤን አስነብቧል፡፡
የፕሮጀክቱ ዋና መሀንዲስ ሊ ያንግ ግንባታው በውሀ ላይ እንደመገንባቱ እንዲሁም ከሚሸፍነው ቦታ ስፋት አንጻር ውስብስብ የኮንስትራክሽን ቅየሳዎችን ቢፈለግም መሳካቱ እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡
ኤርፖርቱን ለመገንባት በ2003 የቦታ መረጣ እና የማሳያ ስራ የተጀመረ ቢሆንም ግንባታው የተጀመረው ከጥቂት አመታት በፊት ነው
አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎች የቻይና የአቪዬሽን እድገት ማሳያ ቁልፍ አካል ናቸው።
ሀገሪቱ አሜሪካን በመብለጥ የዓለማችን ትልቁ የአየር መጓጓዣ ገበያ ማዕከል ለመሆን በመንገድ ላይ ነች።
ዳክሲንግ የተባለው የቤጂንግ ሁለተኛ ግዙፍ አውሮፕላን በ2019 ለአገልግሎት ክፍት ሲሆን የቻይና ባለስልጣናት ሀገሪቱ የአየር ትራንስፖርት ፍላጎትን ለማሟላት በ2035 450 አየር ማረፊያዎች እንደሚያስፈልጓት ተናግረዋል ።