አየር መንገዱ በደንበኞቹ ላይ ለፈጸመው ጥፋት ይቅርታ ጠይቋል
የናይጀሪያ አየር መንገድ መንገደኞችን የተሳሳተ ኤርፖርት ማራገፉ ተገለጸ፡፡
በአፍሪካ ትልቅ የህዝብ ብዛት ባላት ናይጀሪያ ያለው ዩናይትድ ናይጀሪያ የተሰኘው አየር መንገድ መንገደኞችን ካላሰቡት ቦታ አውርዷል፡፡
ተሳፋሪዎቹ ከሌጎስ ወደ አቡጃ ኤርፖርት ለማረፍ በዚህ አየር መንገድ ላይ የጉዞ ትኬት ገዝተው የተሳፈሩ ቢሆንም አሳባ በተባለ ኤርፖርት እንዳረፉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በናይጀሪያ ለደህንነቱ የሰጋ ፓስተር ክላሽ ይዞ መስበኩ አነጋጋሪ ሆኗል
በአቡጃ እና አሳባ ኤርፖርት የ450 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለ ሲሆን የአውሮፕላኑ አብራሪ ስህተቱን እንዴት እንደሰራ አልተገለጸም፡፡
ትናንት ምሽት የተደረገው ይህ በረራ በከባድ አየር ንበረት ምክንያት ወደ አቡጃ መብረር አለመቻሉ የተገለጸ ሲሆን ተሳፋሪዎች ግን አብራሪው አቡጃ ኤርፖርት ደርሳችኋል ውረዱ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
አየር መንገዱ አክሎም ስህተቱ የተፈጠረው የአውሮፕላኑ አብራሪ እና የበረራ አስተናጋጆች ለመንገደኞች የተሰጡት የተለያዩ መረጃ ለስህተቱ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡
ናይጀሪያ ዜጎቿ ከጫካ የሚታደኑ ምግቦችን እንዳይመገቡ አገደች
በኋላም በተደረገ የበረራ ማስተካከያ ሁሉም ተሳፋሪዎች ወደ አቡጃ እንዲበሩ ተደርጓል ተብሏል፡፡
በዚህ የተሳሳተ አውሮፕላን በረራ ወቅት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ሞሃመዱ ቡሃሪ አንዱ ተሳፋሪ ናቸው የተባለ ሲሆን ጉዳዩ በርካቶችን አስገርሟል፡፡