ከ6 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው አዲሱ ኤርፖርት ምን ምን ይይዛል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ለሚያስገነባው ኤርፖርት የዲዛይን ግንባታ ስምምነት ተፈራርማል
ዳር ኩባንያ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባውን ኤርፖርት ዲዛይን ለመስራት የተመረጠ ሲሆን በምን ያህል ክፍያ እንደተስማማ አልተገለጸም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል።
በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው አውሮፕላን ጣቢያ በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚገነባ ገልጿል።
ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ወይም ኤርፖርት የሚገነባው በዓመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን ብቻ የማስተናገድ ያለው ቦሌ ዓከም አቀፍ ኤርፖርትን ለመተካት እንደሆነ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
በቢሾፍቱ ልዩ ስሙ አቡ ሴራ በተባለው ስፍራ የሚገነባው ይህ ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን መቀመጫውን አረብ ኢምሬትስ ያደረገው ዳር የተሰኘው ኩባንያ መመረጡንም አቶ መስፍን ገልጸዋል።
አቶ መስፍን አክለውም አዲሱ ኤርፖርት ግንባታ በአምስት ዓመታት ውስጥ በሁለት ዙር ይገነባል ያሉ ሲሆን ለመጀመሪያው ዙር ግንባታ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደርግበታልም ብለዋል።
ኤርፖርቱ ባንድ ጊዜ አራት አውሮፕላኖችን የማሳረፍ እና መንደርደሪያ መም ይኖረዋል ተብሏል።
270 አውሮፕላኖችን የማሳረፍ አቅም ያለው አዲሱ ኤርፖርት ከቦሌ ኤርፖርት ጋር የሚያስተሳስር ፈጣን ባቡር እና መንገድ እንደሚገነባ ተገልጿል።
ለአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ የሚያስፈልገው ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በብድር እንደሚሸፈን የተገለጸ ሲሆን ብድር ለመስጠት የሚፈልጉ ተቋማት መገኘታቸውንም አቶ መስፍን ተናግረዋል።
ይሁንና የአዲሱን ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን የሚሰራው ዳር ኩባንያ ወጪ ምን ያህል እንደሆነ አቶ መስፍን ከማገር ተቆጥበዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2016 በጀት ዓመት 7ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘ በመግለጽ፤ በዓመቱ 17 ሚሊዮን መንገደኞችንም እንዳስተናገደ ማስታወቁ ይታወሳል።
አየር መንገዱ በትናነትናው እለት በአሜሪካው ፐሬዝዳንት ጆ ባይደን የህይወት ዘመን ሽልማት መሸለሙም ይታወሳል።