ኑሮ ከበደኝ በሚል ለዘጠኝ ወር በኤርፖርት ውስጥ የኖሩት አዛውንት
ግለሰቡ የቤት ኪራይ መክፈል አልቻልኩም በሚል ነበር ኑሯቸውን በኤርፖርት ያደረጉት
ላለፉት ዘጠኝ ወራት በኤርፖርት ሰራተኞች እንክብካቤ ሲደርገላቸው የቆዩት እኝህ አዛውንት በመጨረሻም መንግስት ቤት ሰጥቷቸዋል
ኑሮ ከበደኝ በሚል ለዘጠኝ ወር በኤርፖርት ውስጥ የኖሩት አዛውንት
አርናልዶ የተሰኙት የ83 ዓመት ጡረተኛ ኑሮ ከብዶኛል በሚል ነበር ከሚኖሩባት ሲሲሊ ወደ ቦሎኛ ኤርፖርት የገቡት፡፡
በጡረታ የሚያገኟት ወርሃዊ ተቆራጭ ገንዘብ አልበቃኝም በሚል ወደ ኤርፖርቱ ከገቡ በኋላ አልወጣም ብለው እንደቆዩ ተገልጿል፡፡
የቦሎኛ ኤርፖርት ሰራተኞችም ለእኝህ አዛውንት ምግብ፣ አልባሳት እና ቡና በነጻ ሲያቀርቡላቸው እንደነበር ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ሰራተኞቹ ከዚህ በተጨማሪም በኤርፖርቱ ሚዲያ ላይ በተከታታይ እሳቸውን የሚመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችን ሲያሰራጩ እንደነበርም ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ ወታደሮች ከ77 ዓመት በፊት ከጣልያን የወሰዱትን ኬክ መለሱ
በሰሜናዊ ጣልያን ባለችው ሞዴና ግዛት የባስትግሊያ አስተዳድር እኝህን አባት ለመንከባከብ መወሰኑን ገልጾ መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ሌሎች እንክብካቤዎችን እንደሚያደርግላቸው አስታውቋል፡፡
የቦሎኛ ማህበራዊ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አዛውንቱ ኑሮ ከበደኝ በሚል በቀጥታ ወደ ኤርፖርት ስላመሩ እንጂ አስቀድመው ድጋፍ መፈለጋቸውን ቢነግሩን እንረዳቸው ነበር ብሏል፡፡
በዚህም መሰረት አዛውንቱ ከዘጠኝ ወር የኤርፖርት ህይወት በኋላ ዳግም ወደ ተሸለ ህይወት እንደተመለሱ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡