የቻይና የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ያደረጉት የስልክ ውይይት ያለመግባባት ተጠናቋል
የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታዋንን ከጎበኙ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ቻይና ከቀናት በፊት ማስጠንቀቋ ይታወሳል
የቻይና ጦር ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።
የቻይና ጦር ዌቦ በተሰኘው የሀገሪቱ ማህበራዊ ትስስር ገጹ እንሳሳወቀው ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
የሀገሪቱ 80ኛ ጦር ያወጣውን መገለጫ ዋቢ አድርጎ የሩሲያው አርቲ እንደዘገበው ከሆነ ወደ ጦርነት ለመግባት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
የጦሩ ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን ማስታወቁ የአሜሪካ አፈ ጉባኤ የታይዋን ጉብኝት ምላሽ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።
አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ከቀናት በኋላ በሚገባው ነሀሴ ወር ላይ ታይዋንን እንደሚጎበኙ መግለጻቸው ይታወሳል ።
የአፈ ጉባኤውን የታይዋን ጉብኝት ተከትሎም ቻይና ወታሰራዊ እርምጃዎችን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል መናገሯ አይዘነጋም።
አሜሪካ እና ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከፍተኛ ያለመግባባት ችግር ያለባቸው ሲሆን አሜሪካ ታይዋን የቻይና አካል አይደለችም ስትል ቻይና በበኩሏ ታይዋን የግዛቴ አንድ አካል ናት የሚል ዕምነት አላት።
የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች በዛሬው ዕለት በስልክ የተወያዩ ሲሆን ውይይቱ ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካዋ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥራትን ታይዋንን ለመጎብኘት ማቀዳቸው ሁለቱን ሀገራት ከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ ከቷቸዋል።