ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተከለች
ሚንግሻ በሚባለው የቻይናው አሸዋማ ስፍራ በጎብኚዎች የሚወደድ ሲሆን ግመል ደግሞ ዋነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ነው
ሰሜን ምዕራብ ቻይና ሞቃታማ እና አሸዋማ አካባቢ ነው
ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተከለች፡፡
የዓለማችን ቁጥር ሁለት ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተክላላች፡፡
ሀገሪቱ የግመል ትራንስፖርት መጨናነቅ በሚታይበት ሰሜን ምዕራባዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች ነው፡፡
ጋንሹ ተብሎ የሚጠራው ይህ ግዛት አሸዋማ እና ደረቃማ አካባቢ ሲሆን በዚህ ወቅት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች የሚያዘወትሩት ቦታ ነው፡፡
አካባቢው አሸዋማ በመሆኑ ምክንያትም የግመል ትራንስፖርት ዋነኛ አማራጭ ሲሆን በዚህ ጊዜ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይፈጠር የትራፊክ መብራት ተክላለች፡፡
በዚህ አሸዋማ ስፍራ ከ2 ሺህ 400 በላይ ግመሎች ለትራንስፖርት የተዘጋጁ ሲሆን በየዕለቱ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ወደ ስፍራው እያቀኑ ነውም ተብሏል፡፡
በተለይም ሚንግሻ የሚባለውን ተራራ ለመጎብኘት ጎብኚዎች ይህን አሸዋማ ስፍራ ለማለፍ የግድ ግመልን መጠቀም ግዴታ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የትራፊክ ፖሊስ መስሎ ለወራት በጎዳናዎች ላይ ሲሰራ የቆየው ግለሰብ ታሰረ
አሁን ላይ ሚንግሻ ተራራ በየቀኑ በ20 ሺህ እና ከዛ በላይ ጎብኚዎች እየገበኙት ነው የተባለ ሲሆን ለግመል ትራንስፖርት አቅራቢ ቻይናዊያን ወቅቱ ትልቅ እድል ፈጥሮላቸዋል ተብሏል፡፡
በትራፊክ መብራቱ መሰረትም አረንጓዴ ሲበራ ግመሎቹ የሚጓዙ ሲሆን ቀይ ሲበራ ደግሞ እግረኛ ሰዎች እንዲጓዙ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ቻይናዊያን ሀገራቸውን በመጎብኘት ከሌላው ዓለም የተሻለ ልምድ አላቸው የተባለ ሲሆን በዓለም የሰራተኞች ቀን ብቻ 240 ቻይናዊያን ወደ ሚንግሻ ተራራ ለጉብኝት አምርተዋል ተብሏል፡፡