ህንድ፤ ቻይና በሂማሊያዋ የድንበር ግዛት ያካሄደችውን የቦታዎች ስም ቅየራ ውድቅ አደረገች
ቻይና ተመሳሳይ ውጥረት መፍጠር የጀመረችው ባለፈው አመት በዚሁ ጎዛት ውስጥ የ11 ቦታዎችን ስያሜ በመቀየር ነበር
ህንድ፣ ቻይና በሰሜንምስራቅ ሂማሊያ በምትገኘው አሩናቻል ፕራዴሽ ግዛት ውስጥ ያካሄደችውን የ3ዐ ቦታዎች ስም ቅየራ ተግባር ውድቅ አድርጋዋለች
ህንድ፤ ቻይና በሂማሊያዋ የድንበር ግዛት ያካሄደችውን የቦታዎች ስም ቅየራ ውድቅ አደረገች።
ህንድ፣ ቻይና በሰሜንምስራቅ ሂማሊያ በምትገኘው አሩናቻል ፕራዴሽ ግዛት ውስጥ ያካሄደችውን የ3ዐ ቦታዎች ስም ቅየራ ተግባር ውድቅ አድርጋዋለች።
ይህን የቻይናን እርምጃ "ትርጉም የማይሰጥ" ያለችው ህንድ ግዛቷ የህንድ አካል መሆኑን ተናግራለች።
ቤጂንግ ዛኔጋን በሚል ስያሜ የምትጠራት አሩናቻል ፕራዴሽ የደቡብ ቲቤት አካል ነች የሚል መከራከሪያ ታቀርባለች። ነገርግን ቤጂንግ ይህን አትቀበለውም።
ቻይና ተመሳሳይ ውጥረት መፍጠር የጀመረችው ባለፈው አመት በዚሁ ጎዛት ውስጥ የ11 ቦታዎችን ስያሜ በመቀየር ነበር።
ኑክሌር የታጠቁት የሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ወታደሮች በፈረንጆቹ 2022 መጠነኛ የሆነ ግጭት ውስጥ ገብተው የነበረ ቢሆንም ጥልቅ በሆነ የወታደራዊ እና ዲፕሎማሲዊ ውይይት ውጥረት መርገቡ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ በ2020 በሁለቱ ሀገራት መካከል በምዕራብ ሂማሊያ የተደረገው ወታራዊ ግጭት ግንኙነታቸውን በእጅጉ የጎዳው ሲሆን ይህች ግዛት በተደጋጋሚ የውጥረት መነሻ ነች።
ቻይና ባለፈው ቅዳሜ እንዳስታወቀችው ደቡብ ቲቤት ስትል በጠራችው ቦታ የ30 ቦታዎችን ስም ማስተካካሏን ገልጻለች።
"አዲስ ስም በመስጠት አሩናቻል ፕራዴሽ የማትገሰስ የህንድ አካል እንደነበረች፣ እንደሆነች እና ወደፊትም እንደምትሆን የሚገልጸውን እውነታ አይቀይረውም" ሲሉ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ራንዲር ጄስዋል በዛሬው እለት ተናግረዋል።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰብራማንያም ጄሸንከርም "ስም መቀየር የሚቀይረው ነገር የለም" ብለዋል።
ባለፈው ወር የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በግዛቷ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ለማስመረቅ ማቅናታቸውን ተከትሎ ቻይና ሞዲ በግዛታ ያካሄዱትን እንቅስቃሴ ተቃውማለች። ህንድ ይህን የቻይና ተቃውሞ "መሰረተቢስ" ነው በማለት አጣጥላዋለች።
አሜሪካ አሩናቻል ፕራዴሽን የህንድ ግዛት እንደሆነች እውቅና እንደምትሰጥ እና በግዛቷ ላይ የሚደረግ ወታደራዊ ወረራ በጥብቅ እንደምትቃወም ግልጽ አድርጋለች።