ቻይና ባለፈው ዓመት ከታይዋን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ግንኙነቶችን አቋርጣለች
አሜሪካ እና ቻይና ተቋርጦ የነበረውን ወታደራዊ ግንኙነቶች መልሶ ለማስቀጠል መስማማታቸው ተገለጸ።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጅንፒንግ በተነንታው እለት ፊት ለፊት ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ውይይቱን ተከትሎ በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ሁለቱ ሀገራት በመካከላቸው እየበረታ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ ወታደረዊ ግንኙነቶችም ዳግም ለመመለስ ተስማምተዋል ብለዋል።
ባይደን ትታንት ረቡዕ በካሊፎርኒያ ከቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር የተደረገውን ውይይት ማድረጋውን ተከትሎ "ወደ ቀጥታ፣ ክፍት እና ግልጽ ግንኙነቶች ተመልሰናል" ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ባይደን አክለውም፤ ሁለቱም መሪዎች እርስ በእርሳቸው ቀጥተኛ የግንኙነት መስመር ለመመስረት ተስማምተዋል ብለዋል ።
ቻይና ባለፈው ዓመት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ በኋላ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ግንኙነቶችን አቋርጣ ቆይታለች።
ወታደራዊ ግንኙነቶችን ከማስቀጠል በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የውጥረት መንስኤ በሆኑ አካባቢዎች ሌሎች በርካታ ስምምነቶችን ይፋ አድርገዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጅንፒንግ በአንድ አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተገናኝተው የተወያዩት።
አሜሪካ ከታይዋን ጋር ወታደራዊ ግንኙት ለመፍጠር በተለያየ ጊዜ ፍላጎቷን አሳይታለች። ነገርግን ከታይዋን ጋር ይፋዊ የሆነ ግንኙነት ማድረግ፣ ታይዋንን የራሷ ግዛት አድርጋ ለምትመለከታት ቻይና ቀይ መስመር ነው።
የቀድሞዋ የአሜሪካ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝነት በሁለቱ ሀገራት ታሪክ ከፍተኛ የሚባል ዲፕሎማሲያ ውጥረት መፍጠሩ ይታወሳል።