ወታደራዊ ሚስጥሮችን ለቻይና የሸጠ አሜሪካ ጦር አባል በቁጥጥር ስር ዋለ
የአሜሪካ ጦር የደህንነት ተንታኝ የሆነው ግለሰቡ ወታራዊ ሚስጥርን አሳልፎ በመሸጥ ተከሷል
ሳጅን ኮብሪን ጥብቅ ወታራዊ ሚስጥሮች በ42 ሺህ ዶላር ለቻይና መሸጡ ተነግሯል
የአሜሪካ ጦር የደህንት ጉዳዮች ተንታኝ የሆነው ሳጅን ኮብሪን ሽልዝ ሚስጥራዊ የሆኑ ወታደራዊ መረጃዎች ለቻይና በመሸጥ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።
ሳጅን ኮብሪን ሽልዝ የኤፍ.ቢ.አይ እና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በጋራ ያደረጉትን ምርመራ ተከትሎ ትናንት ሐሙስ በኬንታኪ ፎርት ካምቤል በቁጥጥር ስር መዋሉም ተነግሯል።
በቀረበው ክስ መሰረትም ሳጅን ኮብሪን ለቻይና አሳልፎ በሰጣችው እጅግ ሚስጥራዊ የሆኑ ወታደራዊ መረጃዎች ምትክ 42 ሺህ ዶላር እንደተከፈለው ተመላቷል።
ተከሳሹ መረጃዎች አሳልፎ የመስጠት ወንጅሉን ከሰኔ ወር 2022 ጀምሮ እስከ ታሰረበት ድረስ ሲያከናውን መቆየቱንም ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ሳጅን ሽልዝ የሀገር መከላከያ ቴክኒካዊ መረጃዎችን ያለፍቃድ ወደ ውጭ በመላክ፣ እንዲሁም በመንግስት ላይ በማሴርና ጉቦ በመቀበል ወንጀሎች እንደተከሰሰም ተነግሯል።
ሳጅን ስቸልዝ ለቻይና አሳልፎ ሸጧል ከተባሉት ሚስጥራዊ መረጃዎች መካከልም፤ ስለ ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ምርት እቅድ፣ በዩክሬን ጦርት ላይ የአሜሪካ የወደፊት እቅድ፣ ቻይና ታይዋንን ከወረረች አሜሪካ ስለምትወስደው እርምጃ እና ሌሎችንም ያከተተ ነው ተብሏል።
አፍ.ቢ.አይ በጉዳዩ ላይ በሰጠው አስተያየት፤ “የቀረበው ክስ ግለሰቡ ሀገሩን ለመጠበቅና ለመከላከል የገባው ቃል ኪዳን ላይ ከባድ ክህደት መፈጸሙን ያመለክታል” ብሏል።
የሀገር መከላያ ሚስጠር መጠበቅ ሲገባው ከውጭ ኃሎች ጋር በማሴር እና ሚስጥራዊ መረጃዎች በመሸጥ የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንት አደጋ ላይ መጣሉንም ኤፍ.ቢ.አይ አስታውቋል።