የፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ መመረጥን ተከትሎ ከማኦዜዶንግ በመቀጠል ቻይናን ለረጅም ዓመታት የመምራት ታሪክን ይጋራሉ
ፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲን ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት እንዲመሩ ተመረጡ።
ቻይናን ከፈረንጆቹ 1949 ጀምሮ እያስተዳደረ ያለው የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ የዘንድሮውን ዓመታዊ ጉባኤው አጠናቋል።
ለአንድ ሳምንት የቆየው ይህ የኮሙኒስት ፓርቲ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግን ፓርቲውን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በሊቀመንበርነት እንዲመሩ በመምረጥ ተጠናቋል።
የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከዚህ በተጨማሪም ቻይናን ከፈረንጆቹ 2012 ዓመት ጀምሮ በሬዝዳንትነት እየመሩ ላሉት ሺ ፒንግ ተጨማሪ ስልጣንም እንደሰጠ ሽንዋ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ቻይናን ሲመሩ ከኮሙንስት ፓርቲ ጽንሰ ሀሳብ ባለፈ ለቻይናዊያን ይበጃል የሚሉትን ሀሳብ ወደ ተግባር መቀየር እንዲችሉ ፈቃድም ሰጥቷል።
ፓርቲው 25 አባላት ያሉት የፖሊት ቢሮ እና አዲስ ሰባት የማዕከላዊ አባላት የተመረጡ ሰዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቁም ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ በፓርቲው ጉባኤ መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ለቻይና ድል እንደሚዋጉ እና እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በኮሮና ቫይረስ የ፣ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እየተፈተነ ያለውን ኢኮኖሚ ማስታግስ እንዲሁም የታይዋን ጉዳይ ለፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ ዋነኛ ትኩረት የሚሰጡባቸው ጉዳዮች ናቸው።