ቻይና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ጦር ትገነባለች- ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ
ፕሬዝዳንት ዢ "ደህንነት" የሚለው ቃል 89 ጊዜ መጠቀማቸው አነጋጋሪ ሆነዋል
20ኛው የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ ጉባኤ ለፕሬዝዳንት ዢ ተጨማሪ የስልጣን ጊዜ ይፈቅዳል ተብሎ ይጠበቃል
ቻይና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ጦር ኃይል ግንባታን በማፋጠን ስትራቴጂካዊ የመከላከያ አቅም ትገነባለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ተናገሩ፡፡
ፕሬዝዳንቱ 2 ሺህ300 ገደማ ሚሆኑ ልዑካን በተገኙበትና በቤጂንግ እየተካሄደ ባለው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ቻይና የፓርቲውን ፍጹም ወታደራዊ አመራር ማክበር አለባትም በለዋል፡፡
ያለፉት አምስት አመታት ለቻይና “እጅግ ያልተለመዱና በፈተናዎች የታጀቡ ነበሩ” ያሉት የ69 አመቱ ዢ፣ በየትኛውም ጊዜ ለሚገጥሙን ፈተናዎች ዝግጁ መሆን አለብን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
"በከፍተኛ ንፋስና ከፍተኛ ማዕበል የሚገጥሙን ፈተናዎች ለመቋቋም ዝግጁ መሆን አለብን" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ሁለት ሰአት በፈጀውና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ባተኮረው ንግግራቸው፡፡
ዢ ብሄራዊ ደህንነትን የማስጠበቅ አቅምን ማጠናከር፣ የምግብ እና የኃይል አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን መጠበቅ፣ አደጋዎችን የመቋቋም አቅምን ማሻሻል እና የግል መረጃዎችን መጠበቅ እንደሚገባም በጉባኤው አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንት ዢ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ጉባኤዎች በተለየ መልኩ የቻይና ደህንነት የማረጋጋጥ ጉዳይ በተመለከተ አጽንዖት ሰጥተው መናገራቸውም ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ዢ "ደህንነት" የሚለው ቃል 89 ጊዜ ተጠቅመዋል፤ ይህም በ2017 ከነበረበት 55 ጊዜ እጅግ የበለጠና ለጉዳዩ ትኩረት መስጠታቸው የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡
በተቃራኒው ፕሬዝዳንት "ሪፎርም" የሚለው ቃል በ2017 ከነበረው 68 ወደ 48 ዝቅ ማለቱ አስታውቋል፡፡
ተንታኞች ግን ፕሬዝዳንቱ ለደህንነት ጉዳዮች ትልቅ ትኩረት መስጠታቸው ሌላ አላማ እንዳለው በመናገር ላይ ናቸው፡፡
በሲንጋፖር ናሽናል ዩኒቨርሲቲ የሊ ኩዋን ዩ የህዝብ ፖሊሲ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር አልፍሬድ ዉ ፤ የቻይና ኢኮኖሚ እየቀነሰ ሲሄድ ዢ የህጋዊነትንና ተቀባይነታቸው መሰረት ከኢኮኖሚያዊ እድገት ወደ ደህንነት ለመቀየር እየሞከሩ ነው።
ዉ ሲያብራም "አዲስ ይዘውት መጡት ተረክ - ቻይና ብዙ አደጋዎች ትጋፈጣለች፤ ሀገሪቱ በጦርነት መሰል ሁኔታ ውስጥ ነች፤- እናም አዳኚ እኔ ነኝ በማለት ሰዎች በዙሪያቸው ነው” ብለዋል፡፡
ዢ በስልጣን ላይ በቆየቡቸው አስርት አመታት ለደህንነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በ"ጋራ ብልጽግና" ስም የመንግስትን ኢኮኖሚ መቆጣጠር፣ የበለጠ አስተማማኝ ዲፕሎማሲ እና ጠንካራ ወታደራዊ አቅም በመገንባት ፤ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የምትመራውን ታይዋንን ለመያዝ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ ላይ ተጠምደው መቆየታቸው ይነገራል፡፡
የዘንድሮው 20ኛው የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ ጉባኤ ለፕሬዝዳንት ዢ ተጨማሪ የስልጣን ጊዜ እንደሚፈቅድ የሚጠበቅ ሲሆን ፓርቲው ይሄንን ከፈቀደ ቻይናን ለረጅም ጊዜ በመምራት ከማኦ ዜዶንግ ቀጥሎ ሁለተኛው መሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
በቻይና መዲና ቤጂንግ የተወለዱ ፕሬዝዳንቱ ሲሆን ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ ሀገሪቱን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ይገኛሉ።