በከተማ ውግያ እና በሌሎች ወታደራዊ አግልግሎቶች ጥቅም ላይ ይውላል የተባለው ሮቦት በቅርቡ የቻይናን ጦር ይቀላቀላል
ቻይና አዲስ ያስተዋወቀችው ተዋጊ ሮቦት በአስቸጋሪ የጦርነት ሁኔታዎች ውስጥ የወታደሮችን ህይወት ለመጠበቅ እንደሚውል ይጠበቃል፡፡
አንትሬ አክሲዮስ በተባለ የቻይና ቴክኖሎጂ ኩባንያ የተመረተው ሮቦት እስከ 100ሺ ዶላር እንደሚያስወጣ ተሰምቷል፡፡
ቤጂንግ በቅርቡ ከካምቦድያ ጋር ባደረገችው ወታደራዊ ልምምድ ጥቅም ላይ ያዋለችው ሮቦት ውሻ በጀርባው በተገጠመለት አውቶማቲክ ጠበንጃ ኢላማዎችን በተሳካ ሁኔታ መምታት የሚችል ነው ተብሏል፡፡
በርቀት መቆጣጠርያ የሚሰራው ሮቦት ፈንጆችን ለማነፍነፍ እራሱን ከአደጋ ለመጠበቅም የተገጠመለትን ሰው ሰራሽ አስተውሎት እንደሚጠቀም ታውቋል ፡፡
ቻይና መሰል የኤሌክተሮኒክስ የጦር መሳርያዎችን ስታስዋውቅ ይህ ለመጀመርያ ግዜ አይደለም በባለፈው አመት ከታይላንድ፣ ቬትናም እና ካምቦዲያ ጋር ባደረገችው ወታደራዊ ልምምድ ቅኝቶችን የሚያደርግ ሮቦት ውሻ ጥቅም ላይ አውላ ነበር፡፡
በተመሳሳይ በ2020 የአሜሪካ አየር ሀይል በምድር ላይ ያሉ ኢላማዎችን የሚመዘግብ፣ መረጃዎች የሚሰበስብ እና የጥቃት ስጋትን የሚለይ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ አውሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በቦስተን ዳይናሚክስ የተመረተው የአሜሪካው ሮቦት ከዚህ በተጨማሪም የነፍስ አድን ስራዎችን ለማከናወን እና ለሎጂስቲክ አገልግሎት ጥቅም ላይ መዋል የሚችል እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡
የቤት ውስጥ ስራን ጥንቅቅ አድሮ የሚሰራው “ሮቦት የቤት ሰራተኛ”
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በርካታ ሰው አልባ የጦር መሳርያዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፡፡
በዚህ ውስጥ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ ውስብስብ የሆኑ ወታደራዊ ኢላማዎችን በአየር በምድር እና በሰማይ ለመምታት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት ድሮኖች የቀጣዩ ዘመን የጦር ሰራዊት ዘመናዊነት መለኪያ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡
ቤጂንግ አዲስ ያስተዋወቀቻቸቸው ሮቦት ውሻዎች ደግሞ በምድር ላይ ለሚደረገው ውግያ ከፍተኛ አቅምን እንደሚያላብሱ እየተነገረ ነው፡፡
የዚህ አመት የቻይና ወታደራዊ ወጪ 1.7 ትሪልዮን ዋን ወይም 231 ቢልዮን ዶላር ሲሆን በአምስት አመታት ውስጥ ከፍተኛው ወታደራዊ ወጪ ነው ተብሏል፡፡