ሮቦት በካንሰር ምርመራ ዶክተሮችን መቅደሙ ተነገረ
እንደ እንግሊዙ ጋዜጣ ዘሰን ከሆነ የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች ሮቦት በፋርማሲዎች እና በጤና ማዕከላት ጥቅም ላይ ይውላሉ የሚል ተስፋ አላቸው
ሮቦቱ ስሪዲ ፕሪንተር(3ዲ) በመጠቀም የተሰራ ሲሆን ውጤታማነቱ ከሲልከን በተሰራ 'ጡት' ላይ ተሞክሯል
ሮቦት አደገኛ የተባለውን ካንሰር በመመርመር ዶክሮችን መቅደሙ ተገለጸ።
እንደ እንግሊዙ ጋዜጣ ዘሰን ከሆነ የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች ሮቦት በፋርማሲዎች እና በጤና ማዕከላት ጥቅም ላይ ይውላሉ የሚል ተስፋ አላቸው።
ባለሙያዎቹ ሮቦት በሴቶች ላይ የሚከሰተውን የጡት ካንስር ምርምመራ ስራ ያሻሽለዋል ሲሉ ይናገራሉ።
መሪ ተመራማሪ የሆኑት ጆርጅ ጀንኪሰን እንደተናገሩት የሮቦት ቴክሎሎጂው የጡት ካንስር ለመመርመር የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሚያሟላ እንዲሆን ይፈልጋሉ። የካንሰር ህመምን ሳይዘገይ ወይም በፍጥነት መለየት የመዳን እድልን ከፍ እንዲል ያደርጋል።
ጆርጅ እና ቡድኑ ካንሰርን በመመርመር ከዶክተሮች የተሻለ እና ፈጣን ሮቦት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ጆርጅ እንዳሉት ከሆነ ሮቦት፣ በዶክተሮች እና አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ወይም ሰው ሰራሸ አስተውሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ ዘዴዎችን በመጠቀም በሰው ሊገኝ የማይችል የካንሰር ምልክትን ማግኘት ይችላል።
ይህ ሮቦት ስሪዲ ፕሪንተር(3ዲ) በመጠቀም የተሰራ ሲሆን ውጤታማነቱ ከሲልከን በተሰራ 'ጡት' ላይ ተሞክሯል።
ወደፊት በሚደረግ የካንሰር ምርመራ ሮቦቱ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ጆርጅ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ የተለመደ ቢሆንም አልአልፎ ወንዶችንም ያጠቃል።