የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ታይዋንን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት ቻይናን አስቆጣ
ፕሬዝዳንት ባይደን “የአሜሪካ ጦር ታይዋንን ከቻይና ወረራ ይከላከላል” ብለዋል
ቻይና፤ የጆ ባይደን አስተያየት ዋሽንግተን በታይዋን ላይ ያላትን “ፖሊሲ በእጅጉ የሚጥስ ነው” ብላለች
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በታይዋን ጉዳይ የሰጡት ጉዳይ የሰጡት አስተያየት ቻይናን አስቆጥቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በከሲቢኤስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ጦራቸው ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመከላከል ዝግጁ መሆኑ ተናግረዋል።
ቻይና “ጥቃት ከፈጸመች” የአሜሪካ ኃይሎች ታይዋንን ይከላከላሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁ "ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ጥቃት" ከሆነ “አዎ” ብለው መልሰዋል።
ይህ የጆ ባይደን ምልሽም ታዲያ ታይዋንን እንደግዛቷ አድርጋ የምትመለከታት ቻይናን አስቆጥቷል።
ቻይና፤ የፕሬዝዳንት ባይደን አስተያየት ዋሽንግተን በታይዋን ላይ ያላትን “ፖሊሲ በእጅጉ የሚጥስ ነው” ማለቷ ኤኤፍፒ ዘግቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ “ የፕሬዝዳንቱ አስተያየት አሜሪካ የታይዋን ነጻነትን ላለመደገፍ የገባችውን አስፈላጊ ቁርጠኝነት በእጅጉ የጣሰና ለታይዋን ተገንጣይ የነጻነት ሃይሎች በጣም የተሳሳተ መልእክት የሚያስተላልፍ ነው” ብለዋል።
ዋሽንግተን እንደፈረንጆቹ በ1979 ከታይዋን ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ብታቋርጥም፤በጉዳዩ ላይ ዋሽንግተን ቁርጥ ያለ አቋም ሳትይዝ ለረዥም ጊዜ በዲፕሎማሲያዊ ዥዋዥዌ ተጉዛለች መጓዟንና ታይዋንን በለያየ መልኩ ስታግዝ እንደቆየች ይነገራል።
በቅርቡ የአሜሪካ ምክር ቤት ያጸደቀውና ከታይዋን ጋር ከስምምነት የተደረሰበት የ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ በአሜሪካ ታይዋን መካከል ያለው አጋርነት የሚያሳይ እንደሆነም በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
አሜሪካ ታይዋንን አለሁልሽ እያለቻት ቢሆንም፤ ቻይና ግን አሜሪካ ከከፋፋይ ድርጊቷ ልትቆጠብ እንደሚገባ ስታስጠነቅቅ ይስተዋላል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ በመግለጫቸው "ለሰላማዊ ውህደት እድል ለመስጠት ትልቁን ልባዊ ጥረት ለማድረግ ፈቃደኞች ነን” በማለት አሜሪካ ከባዱን ነገር እየሞከረች እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።
አክለውም "በተመሳሳይ ጊዜ ሀገሪቱን ለመከፋፈል የታለሙ ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን በፍጹም አንታገስም ፤ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድም ምርጫችን የምናስቀምጥ ይሆናል" ብለዋል ቃል አቀባይዋ።