የአሜሪካ ኮንግረስ ባይደን ያቀረቡትን ለታይዋን የሚደረገውን የ1 ነጥብ1 ቢሊዮን ዶላር የመሳሪያ ሽያጭ እቅድ አጸደቀ
ታይዋን "ይህ የጦር መሳሪያ ሽያጭ የታይዋን የረጅም ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅምን ያሳድጋል" ብላለች
በአሜሪካ ኮንግረስ ውሳኔ የተቆጣችው ቻይና ወሳኔው “የታይዋን ስተሬት ሰላምና መረጋጋትን በእጅጉ አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ስትል አስጠንቅቃለች
የአሜሪካ ኮንግረስ ጆ ባይደን የ1 ነጥብ1 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለታይዋን ለመሸጥ ያቀረቡትን እቅድ አጸደቀ፡፡
እቅዱ 60 ጸረ-መርከብ እና 100 ከአየር ወደ አየር የሚተኮሱ ሚሳዔሎችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
የታይዋን ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ቻንግ ቱንሃን በሰጡት መግለጫ አሜሪካ፤ ለታይዋን ደህንነት እና መከላከያ እያደረገች ላለው ቀጣይ ድጋፍ ማማስገናቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል።
"ይህ የጦር መሳሪያ ሽያጭ የታይዋን የረጅም ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅምን ያሳድጋል" ብለዋል ቃል አቀበዩ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ሃገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ታይዋን፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ አካባቢን ደህንነት ለመስጠበቅ ለወሰደቻቸው እርምጃዎች ስታመሰግንም መቆየቷም የሚታወቅ ነው፡፡
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ እና በአካባቢው ያለውን ደህንነትና ሰላም ለመስጠበቅ ለወሰደቻቸው "ተጨባጭ እርምጃዎች" በቅረቡ ማመስገኑ ይታወሳል፡፡
የአሁኑ በአሜሪካ ኮንግረስ የጸደቀው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውሳኔም ታዲያ ለቤጂንግ ሰዎች ጥሩ ዜና እንዳልሆነ በመነገር ላይ ነው፡፡
በተለይም የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውሳኔው በቅርቡ የሰው አልባ አውሮፕላን በታይዋን መመታቱን ተከትሎ የታይዋን-ቻይና ውጥረት ተባብሶ ባለበት ወቅት መሆኑ፤ በምስራቅ ታይዋን እየተስተዋለ ያለውን ወታደራዊ እንቅስቀሴ ወደለየለት የጦር መማዘዝ እንዳይወስደው ተስግቷል፡፡
በአምሪካ የመሳሪያ ሽያጭ ውሳኔ የተበሳጨችው ቻይና ድረጊቱ ሁኔታዎቹን የሚያባብስ ነው ስትል አስጠንቅቃለች፡፡
በዋሽንግተን የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሊዩ ፔንግዩ ፤ የአሜሪካ ድረጊት "ለታይዋን ነጻነት" ተገንጣይ ሃይሎች የተሳሳተ መልዕክት የሚያስተላለፍ እንዲሁም የታይዋን ስተሬት ሰላም እና መረጋጋትን በእጅጉ አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
አክለውም "ቻይና ከሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገባ ህጋዊ እና አስፈላጊ የመከላከያ እርምጃዎችን በቆራጥነት ትወስዳለች" ብለዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻይና፤ አሜሪካ ከዚህ በኋላ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷ ስትገልጽ እንደቆየች የሚታወስ ነው፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ዋሸንግተን በቻይና ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያነጣጠረ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች እንደማይታገስ ገልጿል፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን አሜሪካ፤ ቻይናን ለመያዝ ታይዋንን ከመጠቀም እንድትቆጠብም ማሳሰባቸውም አይዘነጋም፡፡
የአሜሪካ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ፤ ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብርማቋረጧንም እንዲሁ የሚታወስ ነው፡፡