አሜሪካ ሁለት የባህር ኃይል መርከቦቿን ወደ ታይዋን ስትሬት ላከች
የመርከቦቹ መላክ “አሜሪካ የኢንዶ-ፓሲፊክ ቀጠናን ነጻ እና ክፍት ለማድረግ ያላት ቁርጠኝነት ያሳያል” ተብሏል
ጆ ባይደን፤ ቻይና ታይዋንን በተመለከተ ኃይል የምትጠቀም ከሆነ እኛም መጠቀማችን አይቀርም ማለታቸው ይታወሳል
ቻይና በታይዋን ዙሪያ ዙሪያ ታይቶ የማይታወቅ የጦር ልምምዶችን ካደረገች በኋላ ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በታይዋን የባህር አካባቢ ሁለት የአሜሪካ የጦር መርከቦች መጓዛቸውን የአሜሪካ ባህር ኃይል አስታወቀ።
የአሜሪካ ባህር ኃይል ባወጣው መግለጫው፤ ትራንዚቱ “አሜሪካ የኢንዶ-ፓሲፊክ ቀጠናን ነጻ እና ክፍት ለማድረግ ያላት ቁርጠኝነት ያሳያል” ማለቱን ኤፒ ዘግቧል።
ከሶስት ወራት በፊት በቻይና ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሃገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ጆ-ባይደን፤ ቻይና ታይዋንን በተመለከተ ኃይል የምትጠቀም ከሆነ እኛም መጠቀማችን አይቀርምም ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡
እናም አሜሪካ አሁን ላይ የባህር ኃይል መርከቦቿ ወደ ታይወን ባህር ዳርቻዎች መላኳ፤ ሀገሪቱ ለታይዋን ደህንነት የሰጠቸውን ትኩረት እንደሚያመላክት በርካቶች እያነሱ ነው፡፡
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ እና በአካባቢው ያለውን ደህንነትና ሰላም ለመስጠበቅ እየወሰደቻቸው ላሉ "ተጨባጭ እርምጃዎች" ታይዋን እንደምታመሰግን ከሁለት ሳምንት በፊት መግለጻቸውም የሚታወስ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፤የቻይና "ወታደራዊ እና የኢኮኖሚ ዛቻ የዓለም አቀፉን የዴሞክራሲ ካምፕ አንድነት እና ጥንካሬ የበለጠ አጠናክሯል” ብለው ነበር።
የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሴ ፔሎሲ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምታያትን ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ፤ በጉብኝቱ የተበሳጨቸው ቻይና በጣም ግዙፍ የተባለ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጓ ታይዋን ስጋት ውስጥ እንድተወድቅ አድርጓታል፡፡
ይህም በምስራቅ ቻይና ያለው ውጥረት እንደተባባሰና ሁኔታው ወደለየለት የጦር መማዘዝ እንዳያመራ ተሰግቷል፡፡