ቻይና፤ እየተባባሰ ለመጣው ውጥረት “የታይዋን ገዥ ፓርቲ ተጠያቂ ነው” አለች
በቅርቡ የሰው አልባ አውሮፕላን በታይዋን መመታቱን ተከትሎ የታይዋን-ቻይና ውጥረት መባባሱ በመገለጽ ላይ ነው
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የተመታው ሰው አልባ አውሮፕላን የቻይና ስለመሆኑ በግለጽ ያለው ነገር የለም
በቅርቡ የሰው አልባ አውሮፕላን በታይዋን መመታቱን ተከትሎ የታይዋን-ቻይና ውጥረት መባባሱ ቻይና ገለጸች፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ ማንነቱ ያልታወቀው ሰው አልባ አውሮፕላን መመታቱን ተከትሎ ታይዋን ውጥረቱን እየተባባሰ መምጣቱ ለዚህም ታይዋን ኃላፊነቱን ትወስዳለች ሲል ተደምጠዋል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን፤ “ማንነቱ ያልታወቀ ሲቪል ሰው አልባ ሰው አልባ አውሮፕላኑን በጥይት መመታቱን ተከትሎ የታይዋን ገዥ ፓርቲ ውጥረቱን ለማጉላት እየሞከረ ነው”ም ብለዋል።
ቃል አቀበዩ፤ “የዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ ውጥረቶችን ለማጉላት መሞከሩ ምንም ማለት አይደለም” ሲሉም ነው የታይዋን ድረጊት ከቻይና ቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንዳማይችል በሚያመላከት መልኩ መልዕክት ያተላለፉት፡፡
ይሁንና ሃሙስ እለት በቻይና የባህር ጠረፍ አካባቢ በኩል ወደ ታይዋን የአየር ክልል በመዝለቅ ላይ ሳለች የተመታው አውሮፕላን ከቻይና የመጣ ስለመኑናና አለመሆኑ ቃል አቀባዩ በግልጽ ያሉት ነገር እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የታይዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ሱ ጼንግ ቻንግ ፤ ቻይና በምስራቅ ታይዋን የምታደርገው እንቅስቃሴ ካላቆመች እርምጃ እንደሚወስዱ በተደጋጋሚ ሲያስጠነቅቁ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ፕሬዝዳንቷ “የሀገራችንን ሰላም እና መረጋጋት ለመጠበቅ እራሳችንን እንሰጣለን” ያሉበት የቅረቡ አጋጣሚም አይዘነጋም፡፡
የታይዋን ምክትል ኢታማጆር ሹም በበኩላቸው ለኦፕሬሽን እና እቅድ ሊን ዊንሀንግ የታይዋን ብሄራዊ ጦር ራስን የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።