በአሜሪካ በቻይናውያን ላይ የሚፈፀሙ ዘረኝነት ጥቃቶች እየተበራከቱ መሆኑ ተገልጿል
በአሜሪካ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በሀገሪቱ ያለው የደህንነት ሁኔታ ለቻይናውያን ዜጎች አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል።
በመሆኑም አሜሪካ የሚገኙ ቻይናውያን ዜጎች ለግል ደህንነታቸው ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኤምባሲው አሳስቧል።
በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ የሚንፀባረወቅ ጥላቻ እየጨመረ መሆኑንም ሮይተርስ ኤምባሲውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
በቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ የሚፈፀሙ “ተንኮል አዘል” ጥቃቶች የቻይና ዜጎች ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑንም ኤምባሲው አስታውቋል።
የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑ መካከልም በቻይና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን እንደሚገኙበትም ጠቅሷል።
በቻይናውያን ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ መሰል ጥቃቶች በአሜሪካ እየተበራከቱ መሆኑን ያስታወቀው ኤምባሲው፤ በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች በሀገሪቱ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ለግል ደሀንነታቸው ጥንቃቄ እንዲያድርጉ በድረ ገጹ ባወጣው መረጃ አሳስቧል።