ቻይና በሰራችው ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበች
ፀሐዩ ባሳፍነው በግንቦት ወር ለ101 ሰከንድ በ120 ሚሊየን ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት መጠን በመቆየት ክብረ ወሰን አስመዝግቦ ነበር
‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ በከፍተኛ የፕላዝማ ሙቀት ከ1 ሺህ በላይ ሰከንድ መቆየቱ ተነግሯል
የቻይና በሰራቸው ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ ከዚህ ቀደም በራሷ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገቧ ተነገረ።
የቻይና ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ ባለፈው ሐሙስ ለ1,056 ሰከንድ በከፍተኛ የፕላዝማ ሙቀት መቆየት መቻሉንም ነው ሺኑዋ የዜና አገልግሎት የዘገበው።
በዚህም በሙከራ ደረጃ ለረጅም ሰዓት የቆየ በሚል አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገቡን ተነግሯል።
“EAST” የሚል መጠሪያ ያለው ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ ከዚህ ቀደም በግንቦት ወር ላይ ለ101 ሰከንድ በ120 ሚሊየን ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት መጠን በመቆየት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቦ እንደነበረ ይታወሳል።
የሰው ሰራሽ ፀሐዩ ሙከራው የተካሄደው ባለፈው ሳምንት በቻይና የሳይንስ አካዳሚ (ASIPP) ስር በሚገኘው የፕላዝማ ፊዚክስ ተቋም ውስጥ አዲስ የሙከራ ሂደት እንደሚካሄድ መገለጹን ተከትሎ ነው።
እውነተኛውን ፀሃይ በማስመሰል የተሰራው የሰው ሰራሽ ፀሐዩ ሃይድሮጅን እና ዱተሪየም ጋዞችን እንደ ሀይል ማመኝጫ ነዳጅነት በመጠቀም ንጹህ ኢመርጂን ለማመንጨት ታስቦ ዲዛይን መደረጉ ታውቋል።
በዚህ መልኩ የተሰራው “EAST” የሚል መጠሪያ ያለው ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ በ1 ሺህ ሰከንድ ከ100 ሚሊየን ዲጊሪ ሴልሽየስ ሙቀት 1 ሚሊየን አምፒር ከረንት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምንጨት የተያዘውን ግብ ሶስት ግቦች ማሳካቱን ተነግሯል።
አሁን የሚቀረው በአንድ ሙከራ ሁሉን እቅድ ማሳካት ብቻ እንደሆነም ተቋሙ አስታውቋል።
ቻይና ለዓለም አዲስ የሆነው እና ''ሰው ሰራሽ ፀሐይ" የሚል ስያሜ ያለው ይህ ከብክለት ነጻ የሆነ የኑክሌር ማብላያ በፈረንጆቹ 2020 ላይ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።
ሰው ሰራሽ ፀሐዩ ከተፈጥሮ ፀሐይ 13 እጥፍ ያክል ሙቀት ያመነጫል ተብሏል።