ወደ ቻይና ለመግባት የሚፈልግ የየትኛውም ሃገር ዜጋ ከቻይና ሰራሽ ክትባቶች አንዱን እንዲወስድም ተጠይቋል
ቻይና ሊጎበኟት ለሚፈልጉ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች የቪዛ አገልግሎት መስጠት ጀመረች፡፡
ሆኖም ቤጂንግ የትኛውም ወደ ሃገሪቱ መግባት የሚፈልግ ሰው ቻይና ሰራሽ ክትባቶችን እንዲከተብ አሳስባለች፡፡
ከራሷ ውጭ በዓለም ጤና ድርጅት ፈቃድ ያገኙ የትኞቹም ዐይነት ክትባቶችን የተከተቡ ዜጎችንም ጭምር እንደማትቀበል ነው ቻይና ያሳሰበችው፡፡
ይህ ከማሳሰቢያው ጀርባ ሊተላለፍ የተፈለገው ነገር ምንድነው በሚል እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ዜጎቻቸው ወደ ቻይና እንዲገቡ የተፈቀደላቸው አብዛኞቹ ሃገራትም ለቻይና ሰራሽ ክትባቶች የአገልግሎት ፈቃድ አልሰጡም፡፡
ቤጂንግ ከኮሮና ወረርሽኝ መከሰት ጋር በተያያዘ የሚደረጉ የትኞቹንም ዓይነት ጎዞዎች ከልክላ ነበር፡፡
ይህ የተቀዛቀዘ ምጣኔ ሃብቷን ለማነቃቃት ያስችላል፡፡ ሃገራትም በክትባቱና በቪዛ አገልግሎቶች ጉዳይ በጋራ ለመስራት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ቻይና ሰራሽ ክትባቶችን ተከተቡ የሚለው ማሳሰቢያ በ20 ሀጋራት በሚገኙ የቻይና ኤምባሲዎች ይፋ ተደርጓል፡፡
እስካሁንም ቻይና ከሆንግ ኮንግ፣ ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ፣ ከህንድ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከኢራቅ፣ ታይላንድ፣ ክሮኤሺያ፣ እስራኤል፣ ከፓኪስታን እና ከፊሊፒንስ ለሚመጡ ዜጎች በሯን አልዘጋችም እንደ እንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ዘገባ፡፡
ማንኛውም ሰው ወደ ቻይና ከመጓዙ በፊት ቢያንስ ሁለት ጊዜ መከተብ አለበለዚያም የመጀመሪያውን ክትባት የወሰደው ከ14 ባልበለጡ ቀናት ውስጥ እንዲሆን ይጠየቃል፡፡ ክትባቶቹ ቻይና ሰራሽ መሆንም ይጠበቅባቸዋል፡፡