ቻይና አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ገለጸች
አምባሳደሩ ቻይና አረብ ኢምሬትስ በሚቀጥለው ወር በምታዘጋጀው በኮፕ28 ላይ በንቃት ትሳፋለች ብለዋል
አምባሳደር ዛንግ ይሚንግ የኮፕ28 ስብሰባን ለምታዘጋጀው አረብ ኢምሬትስ ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጠዋል
ቻይና አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብር ለውጥን ለመቀነስ የምታደርጠውን ጥረት እንደምትደግፍ የቻይና አምባሳደር ተናገሩ።
በአረብ ኢምሬትስ የቻይና አምባሳደር ዛንግ ይሚንግ የኮፕ28 ስብሰባን ለምታዘጋጀው አረብ ኢምሬትስ ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጠዋል።
በዱባይ የቻይና ቆንሳ መከፈትን አስመልክቶ የቻይና አምባሳደር ለኢምሬትስ ዜና አገልግሎት በላኩት መግለጫ ቻይና አረብ ኢምሬትስ በሚቀጥለው ወር በምታዘጋጀው በኮፕ28 ላይ በንቃት ትሳፋለች ብለዋል።
አምባሳደሩ እይደተናገሩት የሚመለከታቸው የቻይና ባለስልጣናት ከሚመለከታቸው የቻይና ኩባንያዎች ጋር በመነጋገር በዚህ አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
በቻይና እና አረብ ኢምሬትስ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ እየጠነከረ መምጣቱን አምባሳደር ዛንግ ይሚንግ ተናግረዋል።