የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት ጋር ተወያዩ
የአለም ባንክ ፕሬዝደንት አረብ ኢምሬትስን ጎበኙ
የኮፕ28 ስብሰባ በፖሪሱ የኮፕ27 ስብሰባ ላይ የተደረሱ ስምምነቶቸ አፈጻጸም የሚገመገምበት ይሆናል ተብሏል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት ጋር ተወያዩ።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼህ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነሃያን ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት አዳይ ባንጋ ጋር በኮፕ 28 ዙሪያ ተወያይተዋል።
ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ የባንኩን ፕሬዝደንት አጃይ ባንጋን አቡ ዳቢ በሚገኘው አል ሻቲ ቤተመንግስት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ከአየር ንብረት ጉዳይ በተጨማሪ በሌሎች የትብብር ዘርፎች ላይ መክረዋል።
በዚህ አመት በአረብ ኢምሬትስ የምታስተናግደው የኮፕ28 ስብሰባ እና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አደጋ ለመቀልስ ሊደረግ ስለሚገባው አለም አቀፍ ምላሽ ላይም ፕሬዝደንቱ ከባንጋ ጋር ውይይት አድርገዋል።
የኮፕ28 ስብሰባ በፈረንሳይ ፖሪስ በተካሄደው የኮፕ27 ላይ የተደረሱ ስምምነቶቸ አፈጻጸም የሚገመገምበት ይሆናል ተብሏል።