አሜሪካንን ጨምሮ ጥቂት ሀገራት ብቻ የአምስተኛው ትውልድ የጦር አውሮፕላን አላቸው ተብሏል
ባለ ሶስት ሞተሩ አዲሱ የቻይና የውጊያ አውሮፕላን
የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር የሆችው ቻይና በቴክኖሎጂ ዝመና ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራ መካከል አንዷ ናት፡፡
የሀገሪቱ ጦር ስድስተኛው ትውልድ ቴኮኖሎጂ ውጤት የሆነ የውጊያ አውሮፕላን መታጠቁ ተገልጿል፡፡
በቸንገዱ ኤርፖርት የታየው የውጊያ አውሮፕላን የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ ጄ-36 የጠሰኘው የውጊያ አውሮፕላን ሶት ሞተሮች ተገጥመውለት ታይተዋል፡፡
በዓለም ላይ በጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ ተፎካካሪ የሚባሉት አሜሪካ፣ ሩሲያ እና ሌሎችም ሀገራት ባለ ሁለት ሞተር የጦር አውሮፕላን ታጥቀዋል፡፡
የቻይናው ጄ-36 የጦር አውሮፕላን ግን ሰሶት ሞተሮች የተገጠሙለት ሲሆን ከዚህ በፊት ለሚዛን መጠበቅ በሚል ከኋላ በኩል ጭራ መሳይ አካል ያላቸው ሲሆን የቻይናው ግን ከጎን እና ጎን በስተቀር ከኋላ የጠለመደው አካል የለም፡፡
ይህ የውጊያ አውሮፕላን ብዙ መጠኝ ያለው እቃ መጫን እንዲችል፣ ለረጅም ሰዓት ማጥቃት እና የመልሶ ማጥቃት ጥቃቶችን እንዲያመልጥ ተደርጎ መሰራቱን ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ይህ አውሮፕላን ከአንድ ሳምንት በፊት ይፋዊ በረራ ያደረገ ሲሆን የሀገሪቱ መንግስትም የአውሮፕላኑን አጠቃላይ ስሪት የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ መስል እንዲሰራጭ ፈቅዷል ተብሏል፡፡
50 ቶን ክብደት ያለው እቃ የመጫን አቅም አለው የተባለው ይህ የተሻሻለው የጦር መሳሪያ ባለ ሶስት ሞተር ተደርጎ የተሰራው እንደ ድሮን ያሉ የጠላት ኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ለማጥቃት፣ ስርጭታቸው እንዲቋረጥ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መልዕክት መለዋወጫዎችን ለማክሸፍ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡