መኪናዋ ዢ2 የተሰኘችው ሲሆን በኤሌክትሪክ የምትሰራና እና ሁለት መቀመጫዎች ያሏት ነች
የቻይናዋ “በራሪ መኪና” በአረብ ኢምሬትስ በዱባይ የመጀመሪያ በረራ ማድረጓን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በቻይናው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ ዢ ፔንግ ኢንግ የተሰራችው በራሪዋ "መኪና" በዱባይ የመጀመሪያ በረራዋን አድርጋለች፡፡
ኩባንው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ በራሪ መኪኖችን ወደ አለምአቀፍ ገበያ ለማቅረብ በጥረት ላይ መሆኑም ተዘግቧል፡፡
ዢ2 ወይን ዢ ሁለት የተሰኘችው “በራሪ መኪና” በኤሌክትሪክ የምትሰራና እና ሁለት መቀመጫዎች አላት፡፡ መኮናዋ ስምንት አየር የመቅዘፍ የመያስችሉ ክንፎች(ፕሮፔለርስ) እና ተሽከርካሪ ጎማ ያካተተ ቴክኖሎጅ ስራ ታይቶባታል፡፡
አምራች ኩባንያው መኪናዋ ባለፈው ሰኞ ያለሰው ያደረገችውን የ90 ደቂቃ የሙከራ በረራ ለሚቀጥለው የበራሪ መኪና ጄነሬሽን ወሳኝ መሰረት ነው ሲል ገልጾታል፡፡
“ቀስ በቀስ ወደ አለምአቀፍ ገበያው እየገባን ነው” ብለዋል የዢ ፔንግ ኤሮሆት ዋና ስራ አስኪያጅ ሚንጉዋን ኪዩ፡፡ስራ አስኪያጁ እንደተናገሩት ዱባይን የመረጡት ዱባይ በዓለም የፈጠራ ቴክኖሎጅ መዳረሻ ከተማ በመሆኗ ነው፡፡