ሆንግ ኮንግን ከእንግሊዝ የተረከቡት የቀድሞው የቻይና ፕሬዝዳንት አረፉ
ጂያንግ ወደ ስልጣን የመጡት በፈረንጆቹ 1989 በቻይና ቲያንሜን አደባባይ ተከስቶ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ነበር
በተቃዋሚዎች ላይ ክንዳቸውን ያሳረፉት ጂያንግ ሆንግ ኮንግን ከእንግሊዝ የቅኝ ግዛት አስተዳደር መረከብ ችለው ነበር
ቻይናን ከፈረንጆቹ 1989 እስከ 2003 ድረስ ባሉት 14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል ሲል ሽንዋ ዘግቧል፡፡
ጂያንግ ወደ ስልጣን የመጡት በፈረንጆቹ 1989 በቻይና ቲያንሜን አደባባይ ተከስቶ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ነበር፡፡
በተቃዋሚዎች ላይ ክንዳቸውን ያሳረፉት ጂያንግ ሆንግ ኮንግን ከእንግሊዝ የቅኝ ግዛት አስተዳደር የተረከቡ ናቸው፡፡
ጂያንግ ዘሚን በተለይም ቻይና የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን፣ ኦሎምፒክን እንድታስተናግድ እና በኮሚኒስት ፓርቲ ላይ ተነስቶባት የነበረውን ህዝባዊ አመጽ በማብረድ የሀገሪቱ ባለውለታ እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በሰውነት አካል ስራ ማቆም ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ የተነገረላቸው ጂያንግ ዘሚን ቻይና በዓለም መድረኮች ላይ ጎልታ እንድትወጣ እና ከምዕራባዊያን ጋር መልካም ግንኙነቶችን በመመስረትም ይታወቃሉ፡፡
ጂያንግ ዘሚን በቻይና የኢንዱስትሪ መዲና በሆነችው ሻንጋይ ከተማ ከባለቤታቸው እና ሁለት ልጆቻቸው ጋር ይኖሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡