ተራራ ወጪዎች ከሱቋ ለመድረስ 90 ደቂቃ ይወስድባቸዋል
በደቡባዊ ቻይና ሁናን ግዛት ተራራ መሃል ላይ የተስራችው አነስተኛ ሱቅ የበርካቶችን ትኩረት ስባለች።
በግዛቷ ሽንዙያ የተባለው አካባቢ ተራራ የሚወጡ ሰዎች ያዘወትሩታል።
ለነዚህ ተራራ መውጣት ለሚያስደስታቸው ሰዎች የተከፈተችው አነስተኛ ሱቅ የነፍስ አድን ያህል ናት ተብሏል።
ተራራ ወጪዎቹ ድካም ተሰምቷቸው ለአፍታ ቆም ብለው ቀላል ምግብና ውሃ ቢያሻቸው ያለቻቸው ብቸኛ አማራጭ ይህቺው ሱቅ ናት።
ከመሬት 120 ሜትር ኸፍታ ላይ ከተራራ ላይ የተለጠፈችው ሱቅ ውሃ በጣም በርካሽ ዋጋ ታቀርባለች።
2 ስኩዌር ሜትር ስፋት ያላት የተራራ ላይ ሱቅ ብስኩትና ሌሎች ሃይል ሰጪ ምግቦችም ይሸጡባታል።
ሱቋ ከመሬት ከመቶ ሜትር በላይ ከፍ እንደማለቷ የምትሸጣቸው ምርቶች ዋጋ እንደሚያሻቅብ ቢጠበቅም በተመጣጣኝ ዋጋ ነው የምታቀርበው።
በ2018 አገልግሎት የጀመረችው ሱቅ በራሷ የጎብኝዎችን ቀልብ እየሳበች መምጤቷን ሲኤንኤን ዘግቧል።
ተራራ ወጪዎቹ ከአነስተኛዋ ሱቅ ለመድረስ እስከ 90 ደቂቃ ድረስ ሊወስድባቸው እንደሚችል ተገልጿል።
ሪበየቀኑ ወደ ሱቋ እየወጡና እየወረዱ አገልግሎቱን የሚሰጡ ሰራተኞች ጥንካሬም አግራሞትን ፈጥሯል።