ልዩልዩ
የዓለም ትልቁ ተራራ ኢቨረስት "ደረቅ እና ድንጋያማ" እየሆነ መምጣቱን እንግሊዛዊው ተራራ ወጭ ተናገረ
ኬንቶን ኩል ከዓለም አንደኛ የሆነውን ተራራ ለ17ኛ ጊዜ በዚህ ሳምንት መውጣት ችሏል
የ49 አመቱ ተራራ ወጭ 8849 ሜትር ከፍታ ያለውን ተራራ ለመጀመሪያ ጊዜ መውጣት የቻለው በፈረንጆቹ 2014 ነበር
ኬንቶን ኩል የተባለው እንግሊዛዊ ተራራ ወጭ ኢቨረስት በረዶውን እያጣ እና ወደ ደረቅነት እየተቀየረ ነው ብሏል።
ኬንቶን ኩል ከዓለም አንደኛ የሆነውን ተራራ ለ17ኛ ጊዜ በዚህ ሳምንት መውጣት ችሏል።
የ49 አመቱ ተራራ ወጭ 8849 ሜትር ከፍታ ያለውን ተራራ ለመጀመሪያ ጊዜ መውጣት የቻለው በፈረንጆቹ 2014 ነበር።
ኬንቶን ኩል ተራራው እየደረቀ ነው ብሏል።"ወደ 2000ዎቹ ስንመለስ ብዙ በረዶ ነበር"ሲል ክብረወሰን ያሰመዘገበ ቆይታውን ካጠናቀቀ በኋላ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።
ኩል ተራራው ድንጋያማ እየሆነ እና በረዶው እየቀነሰ መሆኑን መመልከቱን ገልጿል።
ከዚህ በፊት ወደ ተራራው በሚወጣቀት ወቅት አሁን ያየውን አይነት ድንጋይ አለማየቱን የገለጸው ኩል አሁን ላይ ግን ተራራው ደረቅ እየሆነ ነው ብሏል።
የአየርንብረት ተመራማሪዎች የመሬት ሙቀት ባለፉት 100 አመታት በአማካኝ በ0.74 በመቶ ጨምሯል።
እንደተመራማሪዎቹ ገለጻ በሂማሊያ አካባቢ ያለው ጭማሪ ከዓለም አማካኝ የሙቀት መጠን መጨመር አማካኝ በላይ ነው ብለዋል።