ቻይና የሰራቻትን ሰው ሰራሽ ጸሀይ ወደ ትግበራ ልታስገባ መሆኗን ገለጸች
ሰው ሰራሿ ጸሀይ ከካርበን በካይ ጋዝ ነጻ እና ሙቀት መስጠት እንደምትችል ተገልጿል
ሰው ሰረሽ ጸሀይ ፕሮጀክት የመጨረሻ ሙከራዋን አድርጋለች
ቻይና ሰራቻትን ሰው ሰራሽ ጸሀይ ወደ ትግበራ ልታስገባ መሆኗን ገለጸች።
የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር ቻይና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰራሽ ጸሀይ መስራቷ ተገልጿል።
ከፈረንጆቹ 2018 ዓመት ጀምሮ ሰው ሰራሽ ጸሀይ ለመስራት ሙከራ ላይ የነበሩት የቻይና ተመራማሪዎች የመጨረሻ ሙከራቸውን እንዳካሄዱ ሽንዋ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ይህች ሰው ሰራሽ ጸሀይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙቀት ማመንጨት መቻሏ የተረጋገጠ ሲሆን ይህብሙቀትም ከካርበን በካይ ጋዝ ነጻ እንደሆነም ተገልጿል።
ቻይና ሰታሿ ጸሀይም በደቡብ ምዕራብ ብሔራዊ የኑክሌር ተቋም ተመራማሪዎች ተሰርታለች የተባለ ሲሆን ብርሀን እና ሙቀትን ማመንጨት ጀምራለች ተብሏል።
ይህ ፕሮጀክት ከቻይና ባለፈ የአሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ጃፓን፣ ሩሲያ፣ ኮሪያ እና ህንድ ተመራማሪዎች ድጋፍ እንዳደረጉም ተገልጿል።
የቻይና ተመራማሪዎች ተሳትፎ ከሁሉም ሀገራት ጥረት ይበልጣል የተባለ ሲሆን ለሙከራ ያህል በ101 ሰከንዶች ውስጥ 120 ሚሊዮን ድግሪ ሴልሺየስ ሙቀት ማመንጨት የቻለች ጸሀይ አድርገዋል ተብሏል።
ይህች ሰው ሰራሽ ጸሀይ በተለይም ምድርን ከበካይ ጋዝ ነጻ የሆነ ሙቀት ለማግኘት ፣ በተወሰኑ መልክዓ ምድሮች ላይ በቂ ሙቀት እንዲፈጠር እና ሌሎች አዳዲስ አገልግሎቶችን ለመፈጸም እንደምትረዳ ተገልጻል።
ሰው ሰራሽ ፀሐዩ ከተፈጥሮ ፀሐይ 13 እጥፍ ያክል ሙቀት ያመነጫል ተብሏል።