ጉላም ሻቢር በዜግነቱ ፓኪስታናዊ ሲሆን በሳውዲ አረቢያ ህይወቱ አልፏል ተብሏል
የዓለማችን ረጅሙ ሰው ህይወቱ አለፈ፡፡
ባንድ ወቅት የዓለማችን ርጅሙ ሰው የነበረው ፓኪስታናዊው ጉላም ሻቢር ህይወቱ እንዳለፈ ተገልጿል፡፡
ከፈረንጆቹ 2000 እስከ 2006 ድረስ የዓለማችን ረጅሙ ሰው ተብሎ በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ስሙ ተመዝግቦ የነበረው ሻቢር በልብ ህመም ምክንያት ህይወቱ አልፏል፡፡
በሳውዲዋ ጅዳህ ከተማ ይኖር የነበረው ጉላህ ሻቢር ለዓመታት በልብ ህመም ሲሰቃይ እንደነበርም ተገልጿል፡፡
ሻቢር በህይወት ዘመኑ 42 ሀገራትን እንደጎበኘ የገለጸ ሲሆን ሳውዲ አረቢያ ለእርሱ ምርጧ ሀገር ናት በሚል እስከ ህይወት ዘመኑ ድረስ ሲኖር ነበርም ተብሏል፡፡
በ1980 በፓኪስታን የተወለደ ሲሆን ቁመቱ 2 ነጥብ 55 ሜትር ርዝመት መድረሱን ተከትሎ ለስድስት ዓመታት የዓለማችን ርጅሙ ሰው ተብሏል፡፡
ቱርካዊው ሱልጣን ኮሰን አሁን ላይ የዓለማችን በህይወት ያለ ረጅሙ ሰው ሲሆን ቁመቱም 2 ነጥብ 51 ሜትር ርዝመት አለው፡፡
አሜሪካዊው ሮበርት ዋድሎው በ2 ነጥብ 7 ሜትር በሰው ልጆች ታሪክ ረጅሙ ሰው ተብሎ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ የሰፈረ ሲሆን በ1940 ህይወቱ እንዳለፈ ተገልጿል፡፡