ፕሬዝደንት ዢ አዲስ የአመራር ቡድናቸውን በታማኞች አዋቅረዋል ተብሏል
ለ3ኛ ጊዜ የስልጣን ዘመን ያሸነፉት የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ አዲሱ ካቢኔያቸውን ታማኞች በሚሏቸው ሰዎች አዋቅረዋል፡፡
የቻይናው ዢ ጂንፒንግ 3ኛ ዙር የስልጣን ዘመን በማሸነፍ የአመራር በድናቸውን በታማኞች ማዋቀራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝደንት ዢ እሁድ እለት ለ3ኛ ጊዜ የስልጣን ዘመን በማግኘት አዲስ የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴን በታማኞች አቋቁመዋል፤ይህም ከማኦ ዜዱንግ በኋላ የሀገሪቱ ኃያል ገዥ መሆን ችለዋል፡፡
ዢን ተከትሎ በታላቁ የህዝብ አዳራሽ መድረክ የወጣው የ63 አመቱ የሻንጋይ ኮሙኒስት ፓርቲ ሃላፊ ሊ ኪያንግ አዲሱን የአመራር ቡድን ተዋውቋል፡፡
ሰባት ሰዎች ያሉት ቋሚ ኮሚቴ፣ የቻይና ከፍተኛ የአስተዳደር አካል ሲሆን ከቀድሞ ኮሚቴ የተመለሱት ዣኦ ሌጂ እና ዋንግ ሁኒንግ እና አዲስ የተሾሙት ካይ ቺ፣ ዲንግ ሹዌሺያንግ እና ሊ ዢ ናቸው። ሊ ኪያንግም ለቋሚ ኮሚቴው አዲስ ናቸው ተብሏል፡፡
የሁሉም የኮሚቴው አባላት እሁድ ላይ እንደገና የማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆኖ ለተሰየሙት የ69 አመቱ ዢ ጂንፒንግ ታማኝ ናቸው ተብሎ ይታሰባል፡፡
አሜሪካ የጄምስታውን ፋውንዴሽን ከፍተኛ ባልደረባ ዊሊ ላም “በኮሚኒስት ፓርቲ ባህል ብርቅ ለሆነው የአንድ አንጃ ያልተለመደ የተገላቢጦሽ ድል ፣ባለፉት ጊዜያት ከባድ የሃይል ሚዛን ይኖራል” ሲል ተናግሯል፡፡