በዩክሬን ከ15 ሺህ በላይ የሩሲያ ወታደሮች መገደላቸውን ሲአይኤ አስታወቀ
የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ወይም ሲአይኤ ስለ ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እና ስለ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግሯል።
የሲአይኤ ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ በኮሎራዶ በተካሄደ የደህንነት ጉባኤ ላይ እንዳሉት ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያካሄደች ባለው ጦርነት 15 ሺህ ወታደሮቿ ተገድለውባታል ብሏል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ኔቶን የመበታተን እቅዳቸው የተሳሳተ እንደነበርም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ዋና ዳፕሬክተሩ ዊሊያም በርንስ አክለውም ፕሬዝዳንት ፑቲን ጤነኛ ለመምሰል እየሞከሩ እንደሆነ እየተወራ ቢሆንም ተቋማቸው ግን ይህንን የሚመለክት መረጃ እንደሌለው አንስተዋል፡፡
የአሜሪካ የስለላ ተቋም ኃላፊ ፑቲንን የተመለከተ መረጃ የሰጡት ሀገራቸው ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ በገለጸችበት ወቅት ነው፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 70ኛ ዓመታቸው ሲሆን አሁን ስላለው ጤንነታቸው አሜሪካ ምንም መረጃ እንደሌላት ተገልጿል፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የሀገራቸው ጦር ኢላማ በምስራቅ ዩክሬይን ብቻ እንደማይወሰን ትናንትና መግለጻቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ የሀገራቸው ጦር ኢላም በምስራቃዊ ዩክሬይን ብቻ እንደማይሆን መግለጻቸው ሞስኮ በሌሎች የዩክሬይን አካባቢዎች ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል ፍንጭ የሰጠ ነው ተብሏል።