ጆ ባይደን፤ የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ ከተካሄደ በኋላ የአፍሪካን መሪዎች ሊያገኙ ነው
በኋይት ሃውስ በሚደረገው ውይይት የአሜሪካና አፍሪካን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተነግሯል
በኋይት ሃውስ በሚደረገው ውይይት የአሜሪካና አፍሪካን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተነግሯል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ ከተካሄደ በኋላ ከአፍሪካ ጋር መሪዎች ጋር ሊወያዩ መሆኑን አስታወቁ።
ባይደን መሪዎቹን በኋይት ሀውስ እንደሚጠሩና በምግብ ዋስትናና በአየር ንብረት ዙሪያ እንደሚወያዩ ገልጸዋል። ውይይቱ በታህሳስ አጋማሽ እንደሚደረግም ነው ጆ ባይደን ይፋ ያደረጉት።
ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው አሜሪካ ለአፍሪካ ያላትን አጋርነትና ወዳጅነት እንደሚሳይም ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈም በኋይት ሃውስ ቤተ መንግስት እንደሚደረግ የሚጠበቀው ውይይት የአሜሪካና አፍሪካን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አንድ ከፍተኛ የዋሸንግተን ባለስልጣን ገልጸዋል ተብሏል።
ይህ ስብሰባ በፈረንጆቹ ከታህሳስ 13 እስከ 15 ቀን 2022 እንደሚካሄድ ተገልጿል። በዚህም መሰረት አዲሱ የፈረንጆች ዓመት 2023 ከመግባቱ በፊትም 50 የአፍሪካ መሪዎች ከጆ ባይደን ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በመሪነት ከተሰየሙ በኋላ እስካሁን አፍሪካን አልጎበኙም።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት፤ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ለመገኛኘትና ለመወያየት ያሰቡት ቻይና በአፍሪካ አህጉር ያላትን ተፅዕኖ ለመገዳደርና ለማሸነፍ እንደሆነ የሚገልጹ አሉ፡፡
ይሁንና ስማቸው ያልተገለጸ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ዋሸንግተን ውይይቱን ያዘጋጀችው ከአፍሪካ ጋር ባላት ወዳጅነት እንጂ ስለ ቻይና ለመምከር እንዳልሆነ ገልጸዋል።
እኝህ የዋሸንግተን ባለስልጣን ፤ የአሜሪካ አጋሮች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው እራሳቸው እንደሚያውቁ ተናግረዋል።
ባለስልጣኑም “ አጋሮቻችን ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አንነግራቸውም፤ አሜሪካ የተሻለ ማሳያ እንደምትሆን እምነታችን ነው፤ ነገር ግን አፍሪካውያን እንዲመርጡን አንቀሰቅስም” ብለዋል።
የአፍሪካ አሜሪካ ጉባዔ ታህሳስ ላይ ከመካሄዱ አስቀድሞ ጥቅምትና ሕዳር ላይ የአፍሪካ ሩሲያ ጉባዔ ኢትዮጵያ ውስጥ ይካሄዳል።
ሩሲያም በዚህ ጉባኤ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እንዲገኙ ጥሪ ማቅረቧ የሚታወሳ ሲሆን ለዚህ ጉባዔም ዝግጅቶች መደረግ ጀምረዋል፡፡
የአፍሪካ ሩሲያ ጉባዔ ሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ልማት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።