ሲአይኤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት እንደታመሙ ተደርጎ በተገለጸው ላይ መረጃ እንደሌለውም ገልጿል
የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ፤ የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እንደታመሙ ተደርጎ እየተናፈሰ ባለው ወሬ ዙሪያ መረጃ እንደሌለው ገለጸ፡፡
አሁን ላይ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ፕሬዝዳንት ፑቲን የጤንነት ችግር እንዳጋጠማቸው እየገለጹ ነው፡፡ የሲአይኤ ዳይሬክተር ዊሊያም በርን፤ የሩሲያው መሪ የጤንነት ችግር እንደገጠማቸው እየተወራ እንደሆነ ገልጸው በዚህ ጉዳይ ግን የደህንነት መረጃ እንደሌለም ገልጸዋል፡፡
ፑቲን ጤነኛ ለመምሰል እየሞከሩ እንደሆነ እየተወራ ቢሆንም ተቋማቸው ግን ይህንን የሚመለክት መረጃ እንደሌለው አንስተዋል፡፡ የአሜሪካ የስለላ ተቋም ኃላፊ ፑቲንን የተመለከተ መረጃ የሰጡት ሀገራቸው ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ በገለጸችበት ወቅት ነው፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 70ኛ ዓመታቸው ሲሆን አሁን ስላለው ጤንነታቸው አሜሪካ ምንም መረጃ እንደሌላት ተገልጿል፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የሀገራቸው ጦር ኢላማ በምስራቅ ዩክሬይን ብቻ እንደማይወሰን ትናንትና መግለጻቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ የሀገራቸው ጦር ኢላም በምስራቃዊ ዩክሬይን ብቻ እንደማይሆን መግለጻቸው ሞስኮ በሌሎች የዩክሬይን አካባቢዎች ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል ፍንጭ የሰጠ ነው ተብሏል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከወጀች በኃላ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ማእቀብ ጥለውባታል፤ ሩሳያ በአጸፋ የጋዝ ፍስት አቋርጣለሁ የሚል ማሰፈራሪያ ስታቀርብ ቆይታለች።